ሁሉን ቻይ የሆነውን አላህን በህልም ማየት ትክክለኛ መገለጥ ነው?
በሃዲስ ቁድሲ እንዲህ እናነባለን፡ “እብን አባስ ነብዩ እንዲህ ሲሉ ሰማሁ ሲል ተረኩ - ‘ዛሬ ሌሊት ጌታዬ (አላህ የተባረከ ይሁን፤ ሥሙም ከፍ ከፍ ይበል) በሚያስደንቅ ግርማ ተገለጠልኝ፡፡’” (Narrated by Imam Ahmad (16026) and Tirmidhi (3159).
አል-ሃፊዝ እንዲህ አለ፤ ኡሌማዎች (ምሁራን) ሁሉን ቻዩን (አላህን) በእሻራ (በህልም) ማየት ይቻላል፤ የእርሱ መገለጥ ደግሞ ሁል ጊዜ ትርጉም ያስፈልገዋል፡፡
አል-ጋዛሊ አላህን በህልም ስለሚያዩት እንዲህ ይላል፡- መለኮትነቱ ምንም አይነት ቅርጽና መልክ አይዝም፡፡ ነገር ግን ለባሪያው ግልጽ የሆነ ገለፃን ተጨባጭ በሆነ የብርሃን ወይም ሌሎች ምሳሌዎች ይገልጣል፡፡ ያ ምሳሌም የአገላለጽ ዘይቤ በመሆኑ እውነተኛ ነው፡፡ ህልም አላሚው፡- አላህን በህልም አየሁት ይላል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ማለት ሌሎች ቁሶችን እንደሚመለከት የአላህን ማንነት ተመለከተ ማለት አይደለም፡፡
አል-ናዋዊ ሳሂ ሙስሊምን ሲያብራራ እንዲህ አለ፡- አያድ እንዲህ አለ፤ ኡሌማዎች አላህን በእሻራ ማየት እንደሚፈቀድ ተስማምተዋል፤ ይህም እውነት ነው፡፡
አል-ባግሃዊ ሻርኅ አል-ሱና በሚለው መጽሐፉ ውስጥ አላህን በእሻራ ማየት ይፈቀዳል በሏል፡፡ አንድ ሰው አላህን በህልሙ ቢያይና እርሱም ጀነት እንደሚገባ፣ ስለ ይቅርታና ከእሳት ስለማምለጥ ተስፋ ቢሰጠው ቃላቶቹና የተስፋ ቃሎቹ ትክክል ናቸው፡፡ አላህ ሲያየው በህልሙ ቢመለከት ምህረቱን ያመላክታል፤ ነገር ግን እያየው ሌላ ቦታ የሚመለከት ከሆነ ስለ ሐጢያት እያስጠነቀቀው ነው ማለት ነው፡፡
ሁሉን ቻይ የሆነውን አላህን በህልም ስለማየት የተሰጡትን አንዳንድ ትርጉሞች ከዚህ በታች አካፍላለሁ፤
- ሁሉን የሚችለውን አላህን በህልም ማየት መልካም ዜናን የሚያመላክትና የእውነተኛ ሃይማኖት ማረጋገጫ ነው፡፡
- ህልም አላሚው አላህን በብርሃን አምሳል ቢያየው ይህ አላህ በፈቃዱ ስለሚያመጣው መልካም ነገር የምሥራች የሚያበስር ዜና ነው፡፡
- አላህ በህልም አላሚውን ቢያናግረው ወይም ቢመለከተው አላህ ምህረትን እንደሚያወርድለትና ጸጋውን በእርሱ ላይ እንደሚያበዛ የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው፡፡
- አንድ ሰው በህልሙ ከአላህ ጋር ሲነጋገር ወይም ወደ እርሱ ቀርቦ ቢያይ ይህ መልካም ነገርን የሚያሳይ ነው ምክንያቱም ይሄ አላህ በዚያ ሰው መደሰቱን ያሳያል፡፡
- አንድ ሰው አላህን በሰው አምሳል በህልሙ ቢያየው ህልሙን ያየው ሰው ጻድቅና ትክክለኛ ሰው መሆኑን ያሳያል፡፡
- አንድ ሰው የአላህን ድምጽ የሚመስል ድምጽ ቢሰማ ህልም አላሚው ታላቅ ስልጣንና ታላቅ ነገር እንደሚያገኝ ያሳያል፡፡
- አንድ ሰው በህልሙ ታላቁ አላህ ስሙን በሰማይ ሲያወሳ ወይም ስሙን ሲጠራው ቢሰማ ይህ አላህ በዚያ ሰው መደሰቱን የሚያሳይ ነው፡፡
- አንድ ሰው በህልሙ አላህ በደስታ፣ በመልካም የምሥራችና በፍስሃ ሲቀበለው ቢያይ ይህ ሰው በትንሳኤ (በዮም አልቅያማ) አላህን እንደሚገናኘው የሚያመላክት ይሆናል፡፡
- አንድ ሰው በህልሙ ሁሉን ቻዩን አለህን ቢያየውና እርሱን መመልከት ከቻለ ያ ሰው በዱንያ መልካም የአላህ ባሪያ እንደሚሆንና በአኬራ ደግሞ ጀነት እንደሚገባ የሚያመላክት ነው፡፡
- አንድ ሰው በህልሙ አላህ ማስጠንቀቂያ ሲሰጠው ቢያይ ያ ሰው ባለመታዘዝ ውስጥ እንዳለና ወደ አላህ ተመልሶ ንስሃ መግባት (መቶበት) እንዳለበት ያሳያል፡፡
- አንድ ሰው በህልሙ በሚያውቀው አካባቢ በአላህ እጅ ራሱን ቢያገኝ ያ አካባቢ በበረካና በመልካምነት የሚሸፈን መሆኑን ያሳያል፡፡ የተጨቆኑት ነጻ ይወጣሉ፤ ጨቋኞችንም ያሸንፋሉ፡፡
- አንድ ሰው በህልሙ በመጋረጃ ውስጥ ተከልሎ አላህን ቢያነጋግረው ህልም አላሚው መልካም ሰው መሆኑና ልቡ ቅዱስ መሆኑን ያሳያል፡፡
- አላህ በእሻራ ለአንድ ሰው ከመጋረጃ በስተኋላ ቢገለጥ በሽተኛ ከሆነ እንደሚፈወስ፣ ከፍርሃት ነጻ እንደሚወጣ፣ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ የልባቸውን ምኞት እንደሚያገኙ የሚያሳይ የምሥራች ነው፡፡
ስለዚህ አላህን በህልም ማየት ይፈቀዳል፡፡ በአላህ ዘንድ ተቀባይነት የማግኘት፤ የጸጋውና የምህረቱ (ረሃማቱ) መገለጫ፤ የሐጢያት ይቅርታ የማግኘት፣ የዚያ ሰው መልካም ሥራ ተቀባይነት ማግኘቱን የሚያሳይ መልካም ዜና ነው፡፡ በተጨማሪም፣ ከበሽታ የመፈወስና ከፍርሃት የመላቀቅ ምልክት ነው፡፡
አላህ ዛሬም በህልምና በራእይ ይናገራል፡፡ የእነዚህን ሕልሞች ትክክለኛ ትርጉም ስንረዳ እንደ ፈቃዱ መኖር እንችላለን፡፡ አሁኑኑ እየተናገረዎት ሊሆን ይችላል፡፡ ምላሽዎት ምንድነው? የህልምዎትን ምንነትና ዓላማ ለመረዳት መጣር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እኛ ደግሞ አላህ የሰጠዎትን ህልም እንዲረዱ ልንደግፍዎት ዝግጁ ነን፡፡