ስሜ ዘይነብ ይባላል፡፡ በኢራን አገር ነው የተወለድኩት፡፡ ገና ልጅ እያለሁ ቤተሰቦቼ ወደ ሌላ አገር ተሰደዱ፡፡ በሰባት አመቴ ሕልም አለምሁ፡፡
ስሜ ዘይነብ ይባላል፡፡ በኢራን አገር ነው የተወለድኩት፡፡ ገና ልጅ እያለሁ ቤተሰቦቼ ወደ ሌላ አገር ተሰደዱ፡፡ በሰባት አመቴ ሕልም አለምሁ፡፡
“አዎን፣ እፈልጋለሁ” አልኩት፡፡
“እርግጠኛ ነሽ ልትከተይኝ ትፈልጊያለሽ?” ብሎ በድጋሚ ጠየቀኝ፡፡
“አዎን፣ እርግጠኛ ነኝ” አልኩት፡፡
ዘወር ብሎ መራመድ ጀመረ፡፡ እኔም ተከተልኩትና ለብዙ ሰዓታት አብረን ተጓዝን፡፡ ረጅም ጉዞ ቢመስልም እኔም ሆንኩ እርሱ አልደከመንም ነበር፡፡
በድንገት ሁለት ወይም ሦስት ሱቆች ከመንገዱ በሌላኛው በኩል ብቅ አሉ፡፡ በሱቆቹ ሰዎች ነጻና የቅንጦት የሆኑ ብዙ ዕቃዎችን ሲያድሉ አየን፡፡ ሱቆቹና በውስጣቸው የነበሩ ዕቃዎች የሚያበሩ፣ የሚያንጸባርቁና የሚያብረቀርቁ ነበሩ፡፡ ብዙ ሰዎች እየገቡ ይወጣሉ፡፡ ሰዎቹ ደስተኞች ይመስሉ ነበር፡፡ እኔም ተሳትፌ እነዚህን ነገሮች ለመውሰድ የሚገፋ ስሜት ተሰማኝ፡፡
እነዚህን ነገሮች ሄጄ ልውሰድ ወይስ አልውሰድ እያልኩ ከራሴ ጋር ሙግት ገጠምኩ፡፡ ብሄድ የሱስ ሊያውቅ አይችልም ምክንያቱም እርሱ ከፍቴ ይሄድ ነበር፡፡ ፈጠን ብዬ ዕቃዎቹን ተቀብዬ በመመለስ የሱስን መከተል መቀጠል እችላለሁ ብዬ አሰብኩ፡፡ በአእምሮዬ ይሄ ከተሰማኝ በኋላ ወዲያዉኑ ሃፍረት ተሰማኝና ዝም በል አልኩት ድምጹን፡፡ ለልቤ፣ አይሆንም አልኩት፡፡ የሱስን እከተላለሁ እንጂ ወደ እነዚያ ሱቆች አልሄድም አለኩኝ፡፡
የሱስ በአአህምሮዬና በሃሳቤ ውስጥ የነበሩትን ነገሮች ሁሉ ያወቀ ይመስል ነበር፡፡ እርሱን ብቻ እንደምከተል ልክ እንደወሰንኩ በአህምሮዬና በልቤ ውስጥ የነበረውን ቃለ ምልልስ የሰማ ይመስል ቆመ፡፡ እኔም ቆምኩኝ፡፡ በአየር ላይ መንሳፈፍ ጀመረ፡፡ ሁለት ጫማ ያክል በአየር ላይ ከፍ ካለ በኋላ ዘወር ብሎ እጁን ዘረጋልኝ፡፡ ወደ እርሱ ቀረብ ብዬ እጁን በመያዝ ከመሬት ከፍ ማለት ጀመርኩ፡፡
ወደ ሰማይ ከፍ እያልን ደመናውንም አልፈን ሰማይ መሆኑን እርግጠኛ ወደ ሆንኩበት ሥፍራ ደረስን፡፡ ሰፊ ነበር፡፡ በአንድ በኩል ብዙ መላእክት ባማረ ድምጽ የአምልኮ መዝሙር እየዘመሩ አላህን ያወድሱ ነበር፡፡ መላእክቱ በጣም ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ ቁጥራቸው ሚሊዮን ይሁን ቢሊዮን መንገር አልችልም፡፡ ድምጻቸው ሰምቼ የማላውቀው አይነት ድምጽ ነበር፡፡ ተቀላቅዬአቸው የአምልኮውን መዝሙር መዘመር ፈለግሁኝ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ካስትል ወይም ቤተክርስቲያን፣ ወይም ቤተመቅደስ የሚመስል ነገር አየሁ፡፡ ሶስቱን ስለሚመስል ምን ብዬ እንደምጠራው ግራ ገባኝ፡፡ ሁሉም ነገር ከወርቅ የተሠራ ነበር፡፡ እያየሁት ኢየሱስን “ያምራል” አልኩት፡፡
“ውስጡን ማየት ትፈልጊያለሽ?” አለኝ፡፡
ውስጡ ያለውን ለማየት በመጓጓት “አዎን” ብዬ በደስታ መለስኩለት፡፡
ወደ ሕንጻው ስንጠጋ ትላልቅ የሆኑ የወርቅ በሮቹ በራሳቸው ተከፈቱ፡፡ ውስጥ ብዙ በወርቅ፣ በከበሩ ድንጋዮችና ጌጣጌጦች የተሞሉ የወርቅ መደርደሪያዎች ነበሩ፡፡
አይኖቼ ከመደርደሪያዎቹ ወደ አስደናቂ ሕንጻው፣ ከዚያም በመስኮት በኩል እየገቡ ወርቄን በአንድነት ወደሚያደምቁ አንጸባራቂ ብርሃን መመልከት ጀመሩ፡፡ ይህ ሕንጻ ወይ ራሱ ብርሃን፤ ወይ ደግሞ ከብርሃን የተሰራ ይመስል ነበር፡፡ የሱስ በሁለት በሮች መካከል ቁሞ ሳለ ወደ እርሱ ዘወር አልኩና “በጣም ያምራል” አልኩት፡፡
ሲያቅፈኝ ያሳየኝን ፈገግታ በሚመስል ፈገግታ ፈገግ አለ፡፡ ፈገግታው ከዚህ በፊት ተሰምቶኝ የማያውቅና በፍጹም የማልረሳው ፍቅርና ሰላም እንዲሰማኝ አደረገ፡፡ ያን ሳስብ ያቺ ቅጽበት እዚያው በቆመችና ባላለፈች ብዬ አስባለሁ፡፡
የሱስ ይህን ሕልም ያሳየኝ በብዙ ምክንያቶች እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ከምክንያቶቹ አንዱ ለሌሎች እንዳካፍልና ሰዎች እንዲባረኩበት ነው፡፡ በዚህ ምስክርነት አላህ በብዙ ልቦች ውስጥ ሊሰራ ይችላል፡፡ በዚህም ሕዝቡን እያዳነ ክብር ያገኛል፡፡