ራሴን እንዳስተዋውቅ ፍቀዱልኝ፤ ስሜ ኢብራሂም ይባላል፡፡ የተከበረው የእምነት አባት በሆነው በነብዩ ኢብራሂም ስም በመሰየሜ እድለኛ ነኝ፡፡ የተወለድኩት በሶርያ ነው፡፡ አሁን ግን ካለው ግጭትና ሃገሬን ካሽመደመደው ጦርነት የተነሳ የምኖረው በሌላ ሃገር ነው፡፡ በቅርቡ ያየሁትን ህልም በቅንነት ከልቤ ላካፍላችሁ እወዳለሁ፡፡
ልቤን በግርምትና በአድናቆት የሞላ ጥልቅና መንፈሳዊ ህልም አለምኩ፡፡ በእንቅልፌ ውስጥ ከጊዜና ስፍራ ባሻገር፣ እውነታና ዘለዓለማዊ ፍስሃ ወደተዋሃዱበት ስፍራ የተወሰድኩ መሰለኝ፡፡ በዚያም ሥፍራ የሰይድና ኢሳን (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) አልዎት (መገኘት) ተመለከትኩ፡፡ በሚያብረቀርቅ ነጭ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡
ትኩር ብዬ ስመለከተው ከውስጡ በመፍለቅ ሰውነቱን የሸፈነው አንጸባራቂ ብርሃን ትኩረቴን ሳበው፡፡ ፊቱ በማይገለጽ ውበት የተሞላና፣ በምድራዊ ቃላት በማይገለጽ መለኮታዊ ነጸብራቅ የበራ ነበር፡፡ በመገኘቱ ውስጥ ሆኜ ጥልቅ የሆነ ሰላምና ፍቅር ተሰማኝ፤ የዚህ ዓለም ስጋትና ሸክም የተወገደልኝ መሰለኝ፡፡
በሰይድና ኢሳ (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ዙሪያ ቁጥር ስፍር የሌላቸው መላዕክት ነበሩ፡፡ ሰማያዊ ግርማቸው በአምልኮታቸው ውስጥ ይነበባል፡፡ በአድናቆት በፊቱ ዝቅ ብለው ይሰግዳሉ፤ በሰማይ አድማስ በሚያስተጋባው ድምጻቸው የምስጋና ዜማ ይዘምሩለታል፡፡ ዜማቸው በአየር ላይ ወደ ላይ አሻቅቦ ወጣ፤ በዙፋኑ ፊት ከነበሩት ከህዝቦችና ነገዶች የደስታ ዜማም ጋር ተዋሃደ፡፡
በሰማዩ ጉባኤ የብዝሃነት ጉራማይሌን አስተዋልኩ፡፡ ከአለም ዙሪያ ሁሉ ሰዎች ለአምልኮ በአንድነት ተጣምረው ነበር፡፡ የቆዳቸው ቀለምና የሚናገሩት ቋንቋ ምንም ተጽህኖ አልነበረውም፡፡ ምክንያቱም በመለኮታዊ አልዎት ፊት ሆነው አንድ ትርታ ነበራቸውና፡፡ ሰይድና ኢሳን (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ካዩ ሰዎች ጉንጭ ላይ የምስጋና እንባ እየጎረፈ የሃሴት ስሜት ከውስጣቸው ፈንቅሎ ሲወጣ ሥፍራው በማይነገር የደስታ ስሜት ተሞልቶ ነበር፡፡
ከዚያም፣ ከጉባኤው መካከል አንድ ረጋ ያለ ድምጽ ጠራኝ፡፡ በፍቅርና በርህራሄ የተሞላ ድምጽ ነበረ፡፡ ሰማያዊውን ዜማ እንድቀላቀል ጋበዘኝ፡፡ በደስታ ተዉጬ ወደፊት እንድራመድ የሚገፋፋ ስሜት ተሰማኝ፡፡ ልቤ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው መለኮት ያለኝን አክብሮትና አድናቆት ለመግለጽ በመፈለግ በሲቃ ተሞላ፡፡
ስጠጋ ከሰይድና ኢሳ (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) በሚፈነጥቅ መለኮታዊ ብርሃን ስሜቶቼ ተማረኩ፡፡ በፊቱም ጥልቅ የእርሱ የመሆን ስሜትና የሕይወት ትርጉም ተሰማኝ፡፡ የተበጣጠሰው ማንነቴም ወደ አንድ የተዋሃደ አንድነት የተለወጠ መሰለኝ፡፡ ሰማያዊው የመዘምራን ቡድን እጃቸውን በመዘርጋት ተቀበሉኝ፡፡ እኔም ድምጼን ከእነርሱ ጋራ አዋህጄ ይህን የማይገለጽ የአንድነት ስሜትና መለኮታዊ ፍቅርን ላላበሰን የምሥጋና ዜማ ዘመርን፡፡
ህልሙ እያለፈ መጥቶ ንጋት ሲቃረብ የዚያን የሰማያዊ ጉባኤ ትዝታን አልረሳሁም፡፡ የተስፋ ምሳሌ በመሆን በሕይወት ተግዳሮቶችና ፈተናዎች መካከል ታላቅ እውነታ እንዳለ አስታወሰኝ፡፡ በዚያ እውነታ ውስጥ ፍቅር ከፍ ብሎ ነግሷል፤ ሁሉም በአምላክ እቅፍ ውስጥ መጽናናትን አግኝተዋል፡፡ በመሆኑም በታደሰ እምነትና በምሥጋና በተሞላ ልብ ጉዞዬን ጀመርኩኝ፡፡ በህልሜ ያየሁትም ጥልቅ መንፈሳዊ ግንኙነት ለዘለዓለም ቀየረኝ፡፡
ህልሙ እያለፈ መጥቶ ንጋት ሲቃረብ የዚያን የሰማያዊ ጉባኤ ትዝታን አልረሳሁም፡፡ የተስፋ ምሳሌ በመሆን በሕይወት ተግዳሮቶችና ፈተናዎች መካከል ታላቅ እውነታ እንዳለ አስታወሰኝ፡፡ በዚያ እውነታ ውስጥ ፍቅር ከፍ ብሎ ነግሷል፤ ሁሉም በአምላክ እቅፍ ውስጥ መጽናናትን አግኝተዋል፡፡ በመሆኑም በታደሰ እምነትና በምሥጋና በተሞላ ልብ ጉዞዬን ጀመርኩኝ፡፡ በህልሜ ያየሁትም ጥልቅ መንፈሳዊ ግንኙነት ለዘለዓለም ቀየረኝ፡፡