ለረጅም ጊዜ ማብቅያ የሌለው በሚመስል ህመም ስሰቃይ ነበር፡፡ ቀናት ወደ ሳምንታት፤ ሳምንታት ወደ ወራት ተሸጋገሩ፡፡ ሰውነቴ ግን ከስቃይና ከህመም እረፍት ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ሐኪሞችና መድሓኒቶች ምንም ሊጠቅሙኝ አልቻሉም፤ ይህ ደግሞ ተስፋ ቢስ እና ልበ-ሰባራ አደረገኝ፡፡ በጨለመብኝ ጊዜ ፈውስ አግኝቼ ጤናዬ እንዲመለስ አጥብቄ ጸለይኩ፡፡
ባለፈው ሳምንት በህመሜ ውስጥ እውነታ የሚመስል ግልጽ የሆነ ህልም አለምኩ፡፡ በህልሙ በጨለማ በተዋጠ ምድረበዳ ውስጥ ቆሜ አየሁ፡፡ የራሴን ተስፋ መቁረጥና ጨለምተኛ ህይወት የሚያሳይ ነበር፡፡ የሚያዝ ነገር ለማግኘት ስታገል በድንገት የሚያንፀባርቅ ነጭ ብርሃን ጨለማውን ዋጠው፤ ከብርሃኑ ውስጥም ከምንም ጋር ሊወዳደር የማይችል ጸጋና ፍቅር የተላበሰ ምስል ብቅ አለ፡፡
ነብዩ ኢሳ (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ከፊት ለፊቴ ቆመ፡፡ መለኮታዊ ርህራሄ ከፊቱ ይነበብ ነበር፡፡ መገኘቱ ብቻ ጨለማንና ፍርሃትን ሁሉ ያስወገደ መሰለ፡፡ በአትኩሮት አይኖቼን ተመለከተ፤ የሚያስደንቅ የሰላምና የተቀባይነት ስሜት ሸፈነኝ፡፡ በእርጋታ ራሴን በእጁ ሲነካኝ ተአምራዊ ትዕይንቶች ይታዩኝ ጀመር፡፡
እጁ ጭንቅላቴን ሲነካኝ የብርሃን ጮራ ከመዳፉ ወደ ሰውነቴ ጎረፈና መላ አካላቴን ሞላው፡፡ የፈውስ ኋይል ያለው ሞቃት ወንዝ በደም ስሬ ውስጥ ያለፈ መሰለኝ፤ በእያንዳንዱ ደቂቃ ህመሜና ስቃዬ እየተወገደ ሄደ፡፡ አካላዊና መንፈሳዊ ፈውስ ማግኘቴን ስረዳ አይኖቼ የምስጋና እምባ አቀረሩ፡፡
በዚያ በተቀደሰ የግንኙነት ጊዜ ነብዩ ኢሳ (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) መቼም ቢሆን በቃላት ሊገለጡ የማይችሉ ነገሮችን ገለጠልኝ፡፡ ፍቅር፣ ተስፋና ሊነቃነቅ የማይችል የህይወት አላማ ገለጠልኝ፡፡ ሕይወቴ ትርጉም እንዳለው፣ መከተል ያለብኝ ጎዳና እንዳለ፣ እና በጉዞዬም ብቻዬን አለመሆኔን የሚነግረኝ መሰለኝ፡፡
ህልሙ ሲቀጥል እንዳወራው እየጋበዘኝ የሱስ እጁን ወደ እነ ዘረጋ፡፡ የእርሱን የፍቅር፣ የርህራሄ እና ሌሎችን የማገልገል ዱካውን እንድከተል አደፋፈረኝ፡፡ የውስጥ ነፍሴን በነካ ድምጹ እንዲህ አለኝ፤ “ተፈውሰሃል፣ ከእንግዲህ ሂድና የተቀበልከውን ብርሃን ለሌሎች አካፍል፡፡ ልክ አንተ በአንድ ወቅት በጨለማ እንደነበርክ ሁሉ፣ በጨለማ ተውጠው ባሉ ሰዎች ላይ ብርሃኑ ይብራ፡፡”
እምባ በጉንጮቼ ላይ እየፈሰሱ ነቃሁ፡፡ በህልሜ ውስጥ ያየሁትን ልምምድ ማስተዋል አቃተኝ፡፡ ነገር ግን ለየት ያለ ነገር እንደተፈጸመ በውስጥ ልቤ አውቄ ነበር፡፡ ለረጅም ጊዜ አቆራምቶኝ የነበረው ህመም ትርጉም ባለው ህይወትና በማይነቃነቅ እምነት ተተካ፡፡
ከዚያ ቀን ጀምሮ ህይወቴ ተቀየረ፡፡ የነብዩ ኢሳን (የእርሱ ሰላም በእኛ ላይ ይሁን) ትምህርት ተቀበልኩ፡፡ እርሱ የሚወክለውን ፍቅርና ርህራሄን ለመላበስ እጥር ጀመር፡፡ በምወስዳቸው እያንዳንዱ እርምጃዎቼ የእርሱ መገኘት እንደሚመራኝ ይሰማኛል፤ የሕይወትንም ተግዳሮቶች መጋፈጥ እንድችል ብርታትና ድፍረት ሰጠኝ፡፡
ለእምነት ተአምራዊ የመፈወስ ኃይልና ወደር የሌለው በፍቅር ለተሞላ የመለከት አልዎት ህያው ምስክር ሆንኩኝ፡፡ ታሪኬን ለሌሎች በማካፈል በሕይወት ተግዳሮቶች ውስጥ ላሉት ሰዎች የተስፋ ጧፍ ሆንኩኝ፡፡ መፈወሴ ለራሴ ጥቅም ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም ሰዎች ህይወት በመንካት መጽናናትና ድፍረት እንዲያገኙ መሆኑን አስተዋልኩ፡፡
ጥርጥር ወይም እርግጠኛ ያለመሆን ስሜት ሲሰማኝ አይኖቼን ጨፍኜ ያን ህልም አስታውሳለሁ፡፡ ያ ህልም ጨለማን በሚያንጸባርቅ ብርሃን የቀየረ ነበር፤ ያ ህልም ነብዩ ኢሳ (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ሲነካኝ ህመሜ የበነነበት ህልም ነበር፤ ያ ህልም በፍቅርና በርህራሄ እርምጃ እንድጓዝ ጥሪ የተቀበልኩበት ህልም ነበር፡፡ ያን ህልም ነው የማስታውሰው፡፡
የፈውስና የመለወጥ ጉዞዬ ይቀጥላል፤ ሕይወቴን ለቀየረው አስገራሚ ግንኙነቱም ዘለዓለማዊ ምስጋና አለኝ፡፡ በአላህ ምህረት ፈውስ፣ የሕይወት ትርጉምና መከተል ያለብኝን ጎዳና አገኘሁ፡፡ ይህም ጎዳና በፍቅር ብርሃን የበራ፣ በነብዩ ኢሳ (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ትምህርቶች የሚመራና በእርሱ አልዎት የተባረከ ጎዳና ነው፡፡