የመሪየም ታሪክ

የአባቴ ሕመም ልቤ ላይ በጣም የከበደብኝ ቀናት በግልጽ አስታውሳለሁ፡፡ በጥልቅ ስጋት የተሞሉ ጊዜያት ነበሩ፡፡ ምንም በማያወላውል እምነት የፈውስ ዱአዎችን አደርግለት ነበር፡፡ በተዓምራዊ መልኩም ይፈወሳል ብዬ ተስፋ አደርግ ነበር፡፡ ነገር ግን ቀናት ወደ ሳምንታት፣ ሳምንታትም ወደ ወራት በተቀየሩ መጠን የአባቴ ሁኔታ ምንም ሳይቀየር ቀረ፡፡ ጥርጣሬ ገባኝ፤ ጸሎቴ ለምን ምላሽ አጣ ብዬ መጠየቅ ጀመርኩ፡፡

አንድ ምሽት በስሜት ውስጥ ሆኜ በወለሉ ላይ ተደፍቼ ወደ አላህ ጮኹኩ፡፡ እንባ በጉንጮቼ እየወረደ “አላህ ሆይ፣ ለምን ጸሎቴን አትመልስልኝም? በችግራችን መካከል አባቴንና እኔን ተውከን? እባክህ ጸሎቴንና ዱዓዬን መልስልኝ!” ብዬ ተማጸንኩኝ፡፡

በዚያ ሌሊት አልጋዬ ላይ ተኝቼ ሳለሁ ለየት ያለ ሕልም አለምኩ፡፡ በጣም የሚያምር ቦታ ውስጥ ቆሜ ለስለስ ባለ ብርሃን ተከብቤ ራሴን አየሁ፡፡ ከዚያም ከብርሃኑ መካከል አንድ የሰው ምስል ብቅ አለ፡፡ እርሱም ነቢዩ ኢሳ አል-መሲህ ነበር (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን)፡፡

ነቢዩ ኢሳ (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ነጭ ልብስ ለብሶ ከፊቴ ቆመ፡፡ ፊቱ ከሌላ ዓለም በሆነው ሰላም ያበራ ነበር፡፡ በፊቱ ቆሜ ጥርጣሬዬና ፍርሃት ሁሉ ጠፍቶ ጥልቅ በሆነ የሠላምና የመጽናናት ስሜት ተተካ፡፡

ወደ እኔ ሲቀርብ ከአይኖቹ ርህራሄ ይነበባል፤ እጆቹን ወደ ሕመምተኛው አባቴ ዘረጋ፡፡ እጁ በቀስታ የአባቴን ግንባር ሲነካ በመላ አካሉ ውስጥ የሙቀትና የፈውስ ንዝረት አለፈ፡፡ የአባቴ ፊት ሲቀየር በመደነቅ ተመለከትኩ፡፡ ፊቱን ሸንተራራማ ያደረገውም ሕመም ጠፍቶ በሠላማዊ ፈገግታ የተተካ መሰለ፡፡

ነቢዩ ኢሳ (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) አይኖቹን ወደ እኔ መለሳቸው፡፡ ለስላሳና የሚስብ ድምጹ ነፍሴን አረካት፡፡ “ውዷ ልጄ መሪየም” አለኝ፡፡ “አባትሽን ፈውሼዋለሁ፡፡ ጸሎትሽ ኃይል እንዳለው አትጠራጠሪ፡፡ ሁሌም የልጆቼን ድምጽ እሰማለሁ፡፡ በጥበቤ ተማመኚ፤ በዕቅዴም እምነት ይኑርሽ፡፡ ስላንቺ ይገደኛል፤ ከአንቺ የሚጠበቀው ተማምነሽብኝ እኔን መከተል ብቻ ነው” አለኝ፡፡ ከዚያም ባረከኝ፡፡

ልቤ እየመታ ከእንቅልፌ ነቃሁ፡፡ በፊቴ የተከናወነውን ተዓምር ማመን አቃተኝ፡፡ በተስፋ ተሞልቼ አንዳች መልካም ነገር ለማየት በመጓጓት ወደ አባቴ መኝታ ክፍል እየተጣደፍኩ ወጣሁ፡፡ ስደርስ በአልጋው ላይ ቁጭ ብሏል፤ አይኖቹ በርተዋል፤ በደስታም ተሞልቷል፡፡ አዲስ የሕይወት ፈቃድ ያገኘ ያክል ነበር፡፡ ለረጅም ጊዜ ያሰቃየው ሕመምም ምንም አሻራ ያሳረፈበት አይመስልም፡፡

በምስጋና ተሞልቼ በጸሎት ወለሉ ላይ ሰገድኩ፡፡ ለአባቴ ስለተሰጠው ተዓምራዊ ፈውስም አመሰገንኩ፡፡ በዚያን ሰዓት የአላህ ቃል ለሆነው ለነቢዩ ኢሳ (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ጥልቅ ምስጋናዬን አቀረብኩለት፡፡ በሕልም እኔን መጎብኘቱ አባቴን መፈወስ ብቻ ሳይሆን ልቤንም በማይነቃነቅ እምነት ሞላው፡፡

ከዚያ ልምምድ ወዲህ እምነቴ አልተነቃነቀም፡፡ ለሚሰሙኝ ሁሉ የአባቴን ተዓምራዊ ፈውስ ታሪክ አካፍላለሁ፡፡ የእርሱ መፈወስ የነቢዩ ኢሳን (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ኃይል፣ የጸሎትን ኃይል፣ የመለኮታዊ ጣልቃ ገብነትና ነቢዩ ኢሳ (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ለሰዎች ሁሉ ያለውን ወደር የለሽ ፍቅርና እንክብካቤ ያሳያል፡፡

የአላህ መንገዶች ከሰዎች ግንዛቤ በላይ መሆኑን ተገነዘብኩ፡፡ መልሶቹም ባልጠበቅናቸው መንገዶች ሊመጡ ይችላሉ፡፡ ለመለኮታዊ ፈቃዱ ራሴን ማስረከብ እንዳለብኝና፣ ገደብ የለሽ ጥበቡን መተማመን እንዳለብኝ ተማርኩ፡፡ ጸሎታችን ሁሌም እንደሚመለሱ ማወቄ ደግሞ ትልቅ መጽናናት ሰጠኝ፡፡

የነቢዩ ኢሳ (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ጉብኝትና የአባቴ መፈወስ የማያቋርጥ የአላህ ምሕረት (ረሃመት) እና በረከት ከአላህ ቸር እጆች እንደሚመነጩ ሁሌም የሚያስታዉሱን ናቸው፡፡ ስለዚህ ጥልቅ ልምምድ ለዘለዓለም አመሠግነዋለሁ፡፡ ምክንያቱም ከመለኮት ጋር ያለኝን ቁርኝት በማጠናከር የእምነትን መንገድ ለመከተል ቁርጠኛ አደረገኝ፡፡

ስለዚህ፣ የአባቴ ተዓምራዊ ፈውስ ታሪኩን የሚሰሙትን ሁሉ መባረኩን ይቀጥላል፡፡ ይህም እምነት ምን ያክል ኃይል እንዳለው፣ የመለኮታዊ ጣልቃ ገብነት እውነተኛነት፣ እንደዚሁም አላህና ቃሉ የሆነው ኢሳ አል-መሲህ (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ወደር በሌለው ፍቅር እንደሚወዱንና እንደሚጠነቀቁልን ያሳያል፡፡

More Stories
ንስሃ (ቶውበት)
አማርኛ