ነጭ ልብስ የለበሰን ሰው በህልም ማየት

ህልሞች በሰዎች ባህል ውስጥ ሁሌም ለየት ያለ ቦታ አላቸው፡፡ አንዳንዴ አህምሮ ደብቆ ያስቀመጣቸውን የምናይባቸው መስኮቶች፣ የፍርሃቶቻችንና የፍላጎቶቻችን መገለጫዎች፣ እና አንዳንዴም መለኮታዊ መልዕክት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በታሪክ ውስጥ ሰዎች ለዘመናት ካዩአቸው ህልሞች መካከል እየተደጋገመ የሚከሰት ህልም አለ፡፡ እሱም ነጭ ለብሶ የሚገለጥ ሰው ነው፡፡ ለብዙዎች ነጭ የለበሰን ሰው በህልማቸው ማየት በጣም ጥልቅ የሆነ የመንፈሳዊና የለውጥ ልምምድ ውስጥ ማለፍ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ነጭ ልብስ የለበሰ ሰው በህልም ሲታይ በሰዎች ህይወት ውስጥ ህልሞቹ ያላቸውን ቦታና ትርጉሞቻቸውን ከእስልምና ባህል አንጻር እንቃኛለን፡፡

ከሚያጋጥሙ የህልም ልምምዶች ነጭ የለበሰ ሰው ህልም የኃይማኖትና የባህል ድንበሮችን የሚሻገር ነው፡፡ ነጭ ልብስ የለበሰን ሰው በህልም የሚያዩ ሰዎች እንደሚሉት ረጋ ያለ፣ ሩሁሩህና ፊቱ የሚያበራ ሰው ሆኖ ልብሱ ንጹህ ነጭ ነው፡፡

እነዚህን ህልሞች የሚያዩ ሰዎች ከአላህ የተላከላቸው መልዕክት ወይም ምሪት አድርገው ነው የሚቀበሉት፡፡ ነጭ የለበሰው ሰው መንፈሳዊ ምክር ይመክራል፤ በእርሱ እንዲያምኑ ያበረታታቸዋል፤ ወይም በግድድሮሽ ውስጥ ያጽናናል፡፡

ነጭ የለበሰ ሰው በህልም ማየት የመንፈሳዊ ፈውስና የይቅርታን እድል ይሰጣል፡፡ ህልሞቹ ይቅርታንና ምህረትን በሚወክለው መለኮት ፊት ንስሃ ለመግባትና መጽናናትን ለማግኘት የሚሰጡ እድሎች ናቸው፡፡

ለአንዳንዶች ነጭ ልብስ የለበሰውን ሰው በህልም ማየት ለመንፈሳዊ ሕይወት ጥንካሬ ጅማሮ ማቀጣጠያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ህልሙ አላሚው እምነቱን እንዲያጠናክር፣ እንዲጸልይ፣ እንዲያሰላስልና ወደ አላህ የበለጠ ለመቅረብ ጥረት እንዲያደርግ ያበረታታዋል፡፡

በህልም ነጭ የለበሰ ሰው ማየት ከአደጋ የመጠበቅና የመደፋፈር ምልክት ነው፡፡ በችግር ውስጥ እያለፉ ያሉ ሰዎች ወይም ግድድሮሽ ያለባቸው ይህን ህልም ሲያዩ ብቻቸውን እንዳልሆኑና ታላቅ የሆነ ኃይል ከላይ እየጠበቃቸው እንደሆነ አድርገው ይተረጉማሉ፡፡

በህልም ነጭ የለበሰ ሰው ኢሳ አል-መሲህን (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ይወክላል፡፡ እርሱን በህልም ማየት ለየት ያለ መንፈሳዊ ልምምድ ነው፡፡ እነዚህ ህልሞች ጠለቅ ያለ መንፈሳዊ አንድምታ አላቸው፤ ምሪትን፣ ይቅርታንና በችግር ጊዜ ረዳት ማግኘትን ያመላክታሉ፡፡ ሀልሞች ብዙ ጊዜ የግል ልምምድ ቢሆኑም፣ ነጭ ልብስ የለበሰውን ሰው በህልም ማየት ግን ለብዙዎች ከአላህ ጋር በጣም የጠበቀና ጥልቅ ግንኙነት የማግኘት ልዩ ዕድልን ያመላክታል፡፡ ለታላቅ እምነት ማረጋገጫ የሚሆን ምስክር ነው፡፡

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  1. السلام عليكم رأيت في منامي رجل يلبس ثوب أبيض طلب مني أن أترك كل شيء وأتبعه لأنه وحده طريق النجاة والجنة. ما تغيير هذا الحلم وشكرا؟

    1. وعليك السلام يا مؤيد نشكرك لمشاركة حلمك معنا. إن ما رأيته في حلمك عن الرجل الذي كان مرتدياً ثوباً أبيض والذي يرمز هذا اللون إلى الطهارة والقداسة هو ما تم ذكره عن سيدنا عيسى المسيح (سلامه علينا) يمكنك قراءة ذلك في الانجيل “وَتَجَلَّى أَمَامَهُمْ، فَشَعَّ وَجْهُهُ كَالشَّمْسِ، وَصَارَتْ ثِيَابُهُ بَيْضَاءَ كَالنُّورِ” (متى 17: 2). ولقد ظهر لك ليخبرك بأنه الوحيد القادر أن يساعدك للوصول للجنة ولكن عليك أولاً اتباع طريقه وتعاليمه لأنه قال “أَنَا هُوَ الطَّرِيقُ وَالْحَقُّ وَالْحَيَاةُ. لَا يَأْتِي أَحَدٌ إِلَى الآبِ إِلّا بِي” (يوحنا 14: 6) لذلك نشجعك أن تبدأ بدراسة الانجبل لأنه سيساعدك في التعرف أكثر عن عيسى المسيح (سلامه علينا) وتعاليمه التي كان يجول بين الناس ويعلمهم عنها. وبالتالي من المؤكد أنك شعرت بالسلام والراحة لأن حضوره يجلب ذلك وهو قد وعد بأنه سياعد كل اللذين يتبعونه ويعطيهم السلام ” سَلاَمًا أَتْرُكُ لَكُمْ. سَلاَمِي أُعْطِيكُمْ. لَيْسَ كَمَا يُعْطِي الْعَالَمُ أُعْطِيكُمْ أَنَا. لاَ تَضْطَرِبْ قُلُوبُكُمْ وَلاَ تَرْهَبْ” (يوحنا 14: 27). لذا يمكنك التواصل معنا في حال كان لديك أي استفسار أو سؤال . بارك الله بك.

  2. Salam, I want to thank you for this article. Short and sweet. I had seen such dreams and I was filled with peace in the presence of the man in white, I believe in him and follow him. Thank you and may Allah bless you.

    1. Aleykum al-salam Salim. We are delighted with your comment and also to hear that you have decided to trust and follow the Man in White. Feel free to write to us if you have any questions or suggestions. May Allah fill your life with blessings.

    1. Thank you, Mufid, for writing and reading the articles on the website. We praise Allah (SWT) that these articles have been a blessing to you. May Allah bless you.

More Stories
ምሳሌዎች
አማርኛ