የምልጃ ሃሳብ በቁርዓን ውስጥ

እስልምናንም ጨምሮ ምልጃ በተለያዩ ኃይማኖቶች ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ቁርዓንም በዚህ ጉዳይ ላይ፣ በተለይ ስለ ኢሳ አል-መሲህ (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን)የሚሰጠው ሃሳብ አለ፡፡ ምልጃ ማለት በሌሎች ሰዎች ፋንታ የመለኮትን ሞገስና ይቅርታ መለመን ነወ፡፡ በሱራ 3፡45 እና 5፡117 ላይ እንደተገለጸው በቁርዓን ውስጥ ኢሳ አል-መሲህ (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) እንደ አማላጅ ልዩ ቦታ ይዟል፡፡

በሱራ አል-ኢምራን (3፡45) መልኣኩ ጅብሪል ስለ ኢሳ አል-መሲህ (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ለማሪያም ሲያስታውቅ በዚህ ምድርም ሆነ በሩቂቱም ዓለም ለየት ያለ መሆኑን አስምሮ ነግሯታል፡፡ የእስልምና ኡሌማዎች በተፍሲር ውስጥ እንደጻፉት ኢሳ አል-መሲህን ልዩ ያደረገው እንደ አማላጅ ያለው ሚና ነው፡፡ ተፍሲር አል-ጃላልያን ላይ እንደተጻፈው፣ ኢሳ (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) እንደ መሲህ በዮም ቂያማ (በፍርድ ቀን) ለታማኝ ተከታዮቹ በመማለድ ይቅርታ እንዲያገኙና እንዲድኑ ያደርጋል፡፡

ሱራ አል-ማኢዳህ (5፡117) በአላህና በኢሳ መካከል በፍርድ ቀን የሚደረገውን ንግግር ይገልጻል፡፡ የኢብን ካቲር ተፍሲር እንደሚያብራራው የኢሳ አል-መሲህ (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ምስክርነት የአማላጅነት ሚናውን ይገልጻል፡፡ አላህን ከልብ ለሚያመልኩት ጠበቃ በመሆ በእነርሱ ፋንታ ሆኖ ይቅርታ ይለምንላቸዋል፡፡

ምልጃ በቁርዓን ውስጥ አከራካሪ ሃሳብ ቢሆንም ከማንነቱ የተነሳ - ነቢይ፣ መሲህ እንደመሆኑ - ኢሳ (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) አማላጅ መሆኑን ብዙ የኢስልምና ኡሌማዎች (ምሁራን) ይስማማሉ፡፡ ሱራ 3፡45 እና 5፡117 ይህንን ሚናውን በመጥቀስ በእርሱ ምልጃ ሙሲሊሞችም የመዳን ተስፋ ሊያገኙ እንደሚችሉ ያሳያሉ፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ የተናገሩት ናቸው የሚባሉ ሐዲዞችም የኢሳ አልመሲህን (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) አማላጅነት ሚኖ ይናገራሉ፡፡ በቂያማ ቀን (በፍርድ ቀን) ለተከታዮቹ ከአላህ ይቅርታን ይለምናል፡፡

ስናጠቃልል፤ ቁርአን ኢሳ አል-መሲህን (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ልዩ አድርጎ የሚመለከት ሲሆን፣ ይህም ደግሞ ኢሳ እንደ አማላጅ ካለው ልዩ ሚና የተነሳ ነው፡፡ ሱራ 3፡45 እና 5፡117 ይሄን ሚናውን ያሳያሉ፡፡ ይህ ደግሞ ሙስሊሞች ከአላህ በኢሳ ምልጃ ይቅርታ እንዲያገኙ ተስፋ ይሰጣቸዋል፡፡ ምልጃ የሚለው ቃል በቁርአን ውስጥ በግልጽ ስራ ላይ የዋለ ባይመስልም ቁርአን፣ ሐዲዝና የኡሌማዎች ትርጉም ኢሳ ለተከታዮቹ አማለጅ ሊሆን እንደሚችል ያመላክታሉ፡፡ ይህ መረዳት ለአላህ የተሰጠን እንዲሆን፣ ለጽድቅና በአላህ ምህረት ላይ ባለን እምነት እንድንጻና ያበረታታናል፡፡

More Stories
The Doctrine of “Son of God” in the Tawrat
አማርኛ