ስሜ ሙስጠፋ ይባላል፡፡ ከመካከለኛው ምስራቅ የመጣሁ ስሆን አሁን ግን በአሜሪካ አገር እየኖርኩ ነው፡፡ ክርስቲያን ሴት አገባሁ፡፡ በደስታ እየኖርን ነበር፤ ከጠንካራ ክርስቲያኖችም ጋር ጥሩ ግንኙነት ፈጠርኩ፡፡ ከዚያም በድንገት ባለቤቴን በደም ግፊት በሽታ አጣኋት፡፡ ጓደኞቼ ሊያጽናኑኝ መጡ፡፡ አቅም ማጣት ተሰማኝ፤ ከሞት ሊያድናት የሚችል የጸሎት ኃይል፤ የማይታይ የሃይል ምንጭ ይኖር እንደሆነበረ አሰብኩ፡፡

ከሞቷ በኃላ ባሉት ወራት ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች ተፈጠሩብኝ፤ ጥልቅ ሃዘን ውስጥም ገባሁ፡፡ በባህድ አገር የሁለት ዓመት ሴት ልጅ ይዤ ያለሰላም ተቀምጨአለሁ፡፡ ክርስቲያን ጓደኞቼ ጉብኝታቸውን ቀጠሉ፤ በሃዘናችንም ተጋመድን፡፡ ብዙ ጊዜ ስለ አላህ እናወራ ነበር፡፡ የኢየሱስን በትር ለመጨበጥ ለየት ያለ ጉዞ ላይ እንደነበርኩ ግልጽ ነበር፡፡ አላህ ለእኔ ታላቅና በግል የሚፈልገኝ መሆኑን ሊያሳየኝ ያስፈልግ ነበር፡፡

ብዙ ሙስሊሞች የአላህን መኖር አይጠራጠሩም፡፡ ጥያቄያቸው ሌላ ነው፡- በአካባቢዬ አለ? በችግሬ ውስጥ ሊረዳኝ ይመጣል? ብዙ ጊዜ ለየት ያሉ የዩቲዩብ ቪዲዮዎችን መመልከት ተያያዝኩኝ፤ በህልሜ ደግሞ ክፉ መናፍስት ያስፈራሩኝ ጀመር፡፡ እኔ ግን አልፈራሁም፡፡

ከዚያም፣ በረመዳን ማለቂያ አካባቢ ለየት ያለ ሕልም አየሁ፡፡ በሕልሜ በአንድ ቤት ውስጥ ነበርኩ ፡፡ እቤቱ ውስጥ ላሞችን የሚዘነጣጥሉ አውሬዎች ነበሩ፡፡ አምስት አውሬዎችና ጅብ የሚመስል ስድስተኛ አውሬ ነበረ፡፡ ነገር ግን መልኩን ቀይሮ የመጣ ሌላ አውሬ ነበረ፡፡ አውሬዎቹን ተመለከትኩና እንዲሄዱ ገፋሁአቸው፡፡ የመጨረሻው አልወጣ አለ፡፡ ስለዚህ ከባድ ምት መታሁት፡፡ ከዚያም በሬዲዮ የሚነገር ድምጽ የሆነ ታላቅ ክስተት በሰማይ ላይ እየተከሰተ ነው ብሎ ሲናገር ሰማሁ፡፡ ስለጉዳዩ የማውቅ፣ ነገር ግን የዘነጋሁ መሰለኝ፡፡

ከቤቱ ወጣሁና ትልቅ ሰዓት የሚመስል በሰማይ ላይ አየሁ፡፡ ትልቀቱ የሕንፃ ያክል ነበር፡፡ የሮም ቁጥሮች ነበሩበት፡፡ ከኃላም ከፊትም ብርሃን በሚያስተላልፍ መስተዋት የተሠራ ነበር፡፡ ከሁሉም አቅጣጫ ሰዎች ወደ ሰዓቱ ይጎርፉ ነበር፡፡ በሰዓቱ ላይ ስንት ሰዓት እንደሚያሳይ ማየት አልቻልኩም፡፡ ነገር ግን በውስጡ የሚሽከረከሩ የሰዓቱ ጥርሶች በግልጽ ይታዩኛል፡፡ ሰዓቱን በሚወክሉ ቁጥሮች ላይ ትንንሽ ሰዎች ሲንቀሳቀሱ አየሁ፡፡

እያየሁ ሳለሁ አንድ ክርስቲያን ጓደኛዬ እጁን በትክሻዬ ላይ አድርጎ የሰዓቱን ቀለም አስታውስ እንደሆነ ጠየቀኝ፡፡ እኔም አዎን፣ ቢጫ ነው አልኩት፡፡ ከዚያም ነቃሁ፡፡

ሕልሙን ልነግራቸው ወደ ክርስቲያን ጓደኞቼ ሄድኩኝ፡፡ በሚገርም መልኩ በሕልሜ ያየሁትን የግድግዳ ሰዓት አየሁ፡፡ ለሁለታችንም የሕልሙን ፍቺ አብረም መፈለግ እንዳለብን የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ እነርሱም ሕልሜን እንድረዳ አገዙኝ፡፡

በሕልሜ ያዩሁት ቤት የመኖሪያና የደህንነት ቦታ ነው፡፡ ነገር ግን ሰላማዊና ለማዳ እንስሳትን የሚበሉ አውሬዎች አሉበት፡፡ ልክ በዩሱፍ ሕልም ውስጥ እንደታየው፣ እርስበርስ የሚባሉ እንስሳት አደጋ እንደሚመጣ የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡

አውሬዎቹ አጥፊዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን በእንስሳቱ መካከል አታላይ የሆነ እንስሳ ነበረ፡፡ ጅቦችና የዱር ድመቶች ሰውን የሚያያጠቁ ሰዎችን የሚወክሉ ናቸው፡፡ ቤቱን በመጨረሻ የለቀቀው አታላዩ አውሬ ሰይጣን ነው፡፡ ስሙም አታላይ ማለት ነው፡፡ ይህን አውሬ ሳባርር ተቋቋመኝ ምክንያቱም ክፉ ስራ እንዲሰሩ ሌሎችን ይቀሰቅስ የነበረው እርሱ ነበር፡፡

በሬዲዮ የሚናገሩ ሰዎች የጊዜውን መቃረብና ስለምልክቶቹ የሚናገሩ የአላህ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ስለ ጊዜው አውቅ ነበር፡፡ በሬዲዮ የሚናገሩት ግን የረሳሁትን ነው ያስታወሱኝ፡፡ እነዚህ የጊዜውን መቃረብ የሚያዉጁና ሰዎችን ወደዚያ የሚያመላክቱ ታማኝ ሕዝቦች ናቸው፡፡

በሕልሜ የነበርኩበት ቦታ ከመሬት ወደ ሰማይ ተቀየረ፡፡ አላህ ምን እያደረገ እንደሆነና እኔ በራሴ ቤቱን ማጽዳት እንደማያስፈልገኝ ሊያሳየኝ ፈለገ፡፡ በወቅቱ አስፈላጊው ነገር ቤቱ ሳይሆን የግድግዳ ሰዓቱ እንደሆነ ነበር፡፡

የግድግዳ ሰዓቱ ጊዜውን የሚያመላክት ነው፡፡ “እርሱም (ዒሳ) ለሰዓቲቱ (ማወቂያ) በእርግጥ ምልክት ነው፡፡ በእርሷም አትጠራጠሩ፡፡ ተከተሉኝም፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው” በላቸው (ቁርዓን 43፡61)፡፡ የግድግዳ ሰዓቱ በኢንጂል ውስጥ የተጻፈውን ያሳያል (ኢንጂል ራዕይ 1፡7)፡፡ “እነሆ፤ በደመና ይመጣል፤የወጉት እንኳ ሳይቀሩ፣ዐይን ሁሉ ያየዋል፤የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከእርሱ የተነሣ ዋይ ዋይ ይላሉ።”

ትርጉሙ ምንድነው? አላህ ጊዜው ቅርብ እንደሆነ እያሳየኝ ነው፡፡ ከምስራቅም ሆነ ከምዕራብ ያሉ ሰዎች እንዲያዩ የግድግዳ ሰዓቱ ብርሃን አስተላላፊ ነው፡፡ ታላቅ ጥቅም እንዳለው በማወቅ ሰዎች ወደ እርሱ ይጎርፋሉ፡፡ በግድግዳ ሰዓቱ ውስጥ የሚታየው የማሽን ጥርስ ደግሞ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲያያዙ የመጡና የአንድ ሕብረት አባል የሆኑ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ተምሳሌት ነው፡፡ በሰዓቱ ውስጥ ነው ታሽገው ያሉት፡፡ ታማኝ ከመሆናቸው የተነሳ የዳኑና የታተሙ ናቸው፡፡ በግድግዳ ሰዓቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች የሚወክሉት በዘመናት መካከል የፍርድ ቀንን የማይፈሩ ሰዎች እንዳሉና በፍርድ ቀን ላይ ስልጣን ያለውን አል-መሲህን ስለተቀበሉ በዚያን ቀንም እንደማያዝኑ ያሳያል፡፡

በመጨረሻም፣ ቀጥተኛይቱ መንገድ ላይ አብሬው እንድጓዝ የተሰጠኝ ጓደኛ አላህ ሰጥቶኛል፡፡ ይህ መንፈሳዊ ወንድም ከእኔ ጋር ወደ አላህ ለማደግ ፍላጎት አለው፡፡ ጊዜው ቅርብ እንደሆነ አላህ አሳይቶኛል፡፡ በግድግዳ ሰዓቱ ውስጥ የአላህ የመጨረሻ ዘመን ሕዝብ አካል መሆን እንደምችል አሳየኝ፡፡ ስለ ኢሳ አል-መሲህና ስለጓደኞቼ እምነት የበለጠ የምማርበት ጉዞ ላይ ነኝ፡፡

More Stories
የነቢዩ ሱሌይማን (ሰሎሞን) ሕልሞች
አማርኛ