ብዙ ሰዎች ሕልም ከአላህ የሚሰጥ ነው ይላሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ሕልም ከሸይጣን ነው ይላሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ መገለጥ (ራእይ) ከአላህ ሲሆን ሕልም ደግሞ ከሸይጣን ነው ይላሉ፡፡ እውነት ነው?
“ሕልሞች ሶስት ዓይነት ናቸው፡- ከአላህ የተላከ ሕልም፤ ከሰይጣን የተላከ የሚያስጭንቅ ሕልም፣ እና ሰው ነቅቶ እያለ በልቡ ያሰበውን መልሶ የሚያልም ሕልሞች ናቸው” (አል ቡኻሪ፤ ሰሂህ ሙስሊም)፡፡
1. 1. ከአላህ የተላኩ እውነተኛ ሕልሞች (الرؤيا من الله): እነዚህ ሕልሞች የሚታዩት በጣም አልፈው አልፈው ነው፡፡ ስውር ትርጉም አላቸው፤ ስለዚህ መተርጎም ያስፈልጋል፡፡ ለሙኢምኖች እነዚህ ሕልሞች የምስራች ነጋሪ ናቸው፡፡ ከክፉ እንዲጠበቁ የሚሰጡ ማስጠንቀቂያም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ወይም ወደፊት የሚፈጸሙ ክስተቶችን የሚያመላክቱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ሁለት ዓይነት እውነተኛ ሕልሞች አሉ፡-
- • ግልጽ (واضح) እና እውነተኛ ሕልሞች፡፡ የማይታየውን የማወቅ ችሎታ ያለው አላህ ብቻ ነው፡፡ ከታላቅ ጥበቡ የተነሳ ከእነዚህ ምስጢሮች አንዳንዶቹን ለሚሻ ሰው ይገልጣቸዋል፡፡ እነዚህ ትርጉም አያስፈልጋቸውም፡፡ እነዚህ አይነት ሕልሞች አጭር፣ ቀጥተኛ እና በራሳቸው የተተረጎሙ ናቸው፡፡ ሕልሞች በምልክቶች የተሞሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ጌታ በምልክት፣ በምሳሌ፣ እና በታሪክ መናገር ደስ የሚያሰኘው ይመስላል፡፡ ውበቱን በአህምሮአችንና በልባችን ላይ ለመሳል ምሳሌያዊ ቋንቋዎችን ይጠቀማል፡፡
- • ምስጢራዊ (مرموز) የሆኑ እውነተኛ ሕልሞች ግልጽ መገለጥ ስላልሆኑ ትርጉም ያስፈልጋቸዋል፡፡ እንደዚህ ያሉ ሕልሞች የመገለጥ ዕውቀት ያስፈልጋቸዋል፤ ስለሆነም ሕልም የመፍታት ጸጋ ባላቸውና መገለጥን ለማግኘት አላህን መቅረብ በሚያውቁ ሰዎች መተርጎም አለባቸው፡፡ ከባድ ሕልም ሲያጋጥም ምስጢርን ሁሉ መግለጥ ከሚችል አምላክ ጋር እንድንገናኝ የቀረበ ጥሪ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡
መልካም ሕልሞችን ስናልም የሚከተሉትን ማድረግ አለብን፡-
- • ለመልካሙ ሕልም አላህን ማወደስና ማመስገን
- • ደስተኛ መሆን
- • አላሚው ለሚወዳቸውና ለሚያምናቸው ሰዎች ህልሙን ማውሳት
2. Self Talk 2. የራስ ሕልም (حديث النفس)፡- ስለሚያሳስቡን ጉዳዮች ወይም አህምሮአችንን የሚይዙ ነገሮችን በተመለከተ የምናልማቸው ሕልሞች፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሕልሞች የውስጥ ሐሳቦቻችንና የስጋቶቻችን መገለጫዎች ስለሆኑ ትርጉም አያስፈልጋቸውም፡፡
3. 3. ከሰይጣን የሆኑ ሕልሞች (الحلم من الشيطان)፡- ነቅተን እያለን ብቻ ሳይሆን በእንቅልፋችንም ጠላታችን ሰይጣን ያውከናል፡፡ እነዚህ አዋኪ ሕልሞች ከሰይጣን ናቸው፡፡ ሊያስፈራራንና ሊያስደነግጠን ዓላማ ያደርጋል፤ ምክንያቱም ኀይላችንና ጥንካሬያችን በልባችን ውስጥ እንዳሉ ያውቃል፡፡ እምነታችንን ሊያደክም ይፈልጋል፤ አላህን ከማምለክ እንድንደክም ሐዘንተኞች ሊያደርገን ይፈልጋል፡፡
መጥፎ ሕልሞችን ስናይ የሚከተሉትን ማድረግ አለብን፡-
- • በሕልሙ ከተገለጠ ክፉ ለማምለጥ ወደ አላህ መሸሽ
- • ከሰይጣን ክፋት ወደ አላህ መሸሽ
- • ሕልሙን ለማንም አለመናገር (ስለማይጎዳ ዝም ማለት)
- • መጸለይና የአላህን ከለላ መፈለግ ይመከራል፡፡
ምንም ዓይነት ሕልም ቢያልሙ ይጻፉልን፤ ልንረዳዎት ዝግጁ ነን፡፡