“Perfuming the Sleep in the Expression of a Dream” በሚል መጽሐፏ ውስጥ ነቡሉሲ “ማንም ሙስሊም በህልሙ የኢንጂልን መጽሐፍ ቢያይ ለአምልኮና ለምነና የተሰጠ እንደሆነ ያመላክታል፡፡ ምናልባትም ኢንጂል መለየትን ያመላክታል፡፡ ህልም አላሚው ተጽህኖ ሊያሳድር የሚችል ወይም ሃይል ያለው ሰው ከሆነ ያየው ራዕይ ወይም ህልም ጠላቶቹ እንደሚጨቆኑ ወይም ቅሬታ እንደሚወገድ ያሳያል” ብላለች፡፡
ኢንጂልን(ወንጌልን) በህልም ማየት ሰብአዊ መልዕክትን ወይም ኃላፊነት መወጣትን ያመላክታል፡፡ እነዚህ ኃላፊነቶች ፈታኝ ሊሆኑ ይችላሉ ምክንያቱም ኢንጂል ኢሳ አል-መሲህ (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) መልዕክቱን ለዓለም ሲያውጅ የተቀበለውን መከራ ያወሳል፡፡ በህልም ኢንጂልን መግዛት ደግሞ በጣም ጠቃሚ ወይም ሰፊ እውቀት ማግኘትን የሚያሳይ ሊሆን ይችላል፡፡
ኢንጂል በቤት ውስጥ ተቀምጦ ማየት ደግሞ ቤቱ በቅርብ ጊዜ መልካም ዜናን እንደሚመሰክር ያመላክታል፡፡
ህልም እንጂልን ማየት ለአላሚው መልካም ዜና ነው፡፡ አንድ ይሆናል ብለው ተስፋ የሚያደርጉት ነገር ካለና በህልም ወንጌልን ካዩ፣ ተስፋው ይፈጸማል ማለት ነው፡፡
በቀደምት አተረጓጎሞች ኢንጂልን በህልም ማየት ከስጋትና ከሀዘን የመዳን ምልክት ነው፡፡ በመሆኑም፣ አንድ የተጨነቀ ሰው በህልሙ ኢንጂልን ሲያነብ ወይም ሲያገላብጥ ቢያይ ከስጋት፣ ከስቃይና ከሀዘን ያመልጣል ማለት ነው፡፡
በሽተኛ ሰው በህልሙ ኢንጂልን ቢያይ እንደሚድን ያሳያል፡፡ የታመመ/ች ሰው በህልም ኢንጂል ይዞ/ዛ ቢያይ/ታይ በአላህ ረሃማት (ምህረት) ይድናል/ትድናለች ማለት ነው፡፡
ኢንጂልን በህልም ማየት ቃልኪዳንን ያመላክታል፡፡ ኢንጂል ከመጽሐፍ ቅዱስ አዲስ ኪዳንን የሚያካትት ስለሆነ አዲስ ኪዳን (ቃልኪዳን) የሚለው ቃል ጠቃሚ ለውጥን ወይም ጠቃሚ ተሃድሶን ያመላክታል፡፡
በመገለጥ ኢንጂልን ማየት ትዕግስትን፣ እረፍትንና ሠላምን የሚያመላክት ስለሆነ ኢንጂል ይቅርታ ማግኘትን ይወክላል፡፡
በህልም ኢንጂልን ማየት ብዙ ነገሮችን ያመላክታል፤ ብዙ ትርጉሞችም አሉት፡፡ ኢንጂልን በተመለከተ የሚሰጡ አብዛኞቹ አተረጓጎሞች በንግርትና በተግባር ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ ኢንጂል የሚለው ቃል ከግሪክ ሥረው-ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም መልካም ዜና ወይም የምሥራች ማለት ነው፡፡
ቃሉ ካለው ትልቅ ቦታ የተነሳ ኢንጂልን በህልም ማየት አዎንታዊ ትርጉሞች አሉት፡፡ የመልካምና አስደሳች ዜና ምልክት ሲሆን ከሞላጎደል መልካም ለውጥ በአላሚው ህይወት ውስጥ እንደተከናወነ ያሳያል፡፡ ኢንጂል ማለት አዲስ ኪዳን ነው፤ ስለዚህ በህልም ኢንጂልን ማየት የሚያሳየው በመንፈሳዊ ህይወት፤ ማህበራዊ እርከን፣ እንደዚሁም በኑሮና በሌሎችም ነገሮች ተሃድሶን ማግኘትን ያመላክታል፡፡
ቅዱስ መጽሐፍ መሆኑን በመገንዘብ ኢንጂልን ከሚሰጠው አገልግሎት አንጻር ስናይ፤ በህልም ኢንጂልን ማየት ደህንነትና ትድግናን ያመላክታል፡፡ ምክንያቱም ይህ መጽሐፍ የኢሳ አል-መሲህን (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ጉዞ ከመወለዱ እስከ ስቅለቱና በሦስተኛ ቀን እስከ መነሳቱ የሚያሳይ ስለሆነ ነው፡፡ እርሱ ወደዚህ ዓለም የመጣው ኃጢአተኛን ሰው ለማዳን ነውና፡፡
ኢንጂልን በህልም ማየት አላሚው ከኃጢያትና ከስህተት መዳኑን የሚያመላክት ነው፡፡ ኢንጂል ከበሽታና ከህመም የመፈወስ ምልክትም ነው፡፡ መንፈሳዊና ሞራላዊ (ግብረገባዊ) ለውጥንም የሚወክል ነው፡፡ ምክንያቱም በእርግጠኝነት ሊሆን ያለውን የእውነተኛ ቃልና መልካም ዜና ትርጉም ስለሆነ ነው፡፡
በአንዳንድ ቀደምት ትርጉሞች በህልም ኢንጂልን ማየት ድነትን ያመላክታል፤ እንደዚሁም ክስና ክርክር ላይ ላሉ ሰዎች ትክክለኛ ስለመሆናቸው የሚመሰክር ነው፡፡ ህልም አላሚው ኢንጂሉ በአረብኛ ቋንቋ ተጽፎ ቢያይ ያ ሰው/ያቺ ሴት ለእውነት፣ ለፍትህና ለእኩልነት የሚመሰክር/የምትመሰክር ሰው ነው/ ነች ማለት ነው፡፡
ኢንጂልን በመገለጥ የሚያይ ህመምተኛ ሰው ፈውስ እንደሚያገኝ ያሳያል፤ ለተጨነቀ፣ ላዘነ፣ ቅን ሆኖ ለታሰረና መፈታትን ለሚፈልግ ሰው መልካም ዜና እንደሚሰሙ ያመላክታል፡፡ ለኡሌማዎችና ለመምህራን ኢንጂልን በህልም (በመገለጥ) ማየት የአላሚውን ጥበብና እውቀት ያሳያል፡፡ ማንም ሰው በህልም ኢንጂልን ሲያነብ ቢያይ በኃይማኖት ጉዳይ ምሁር መሆኑን ወይም ለህዝብ የሚጠቅም ትምህርት እንደሚማር ያሳያል፡፡ ኢንጂል የሚያስደስትና የምሥራችን የሚወክል ነው፡፡
ኢንጂልን ለማንበብና የበለጠ ስለኢንጂል ለመማር ሰፊ ጊዜ ብትወስድ ትባረካለህ/ትባረኪአለሽ፡፡ የኢንጂልን ቅጂ በዚሁ ደረ-ገጽ ላይ (source) በሚለው ርዕስ ሥር ልታገኝ ትችላለህ/ትችያለሽ፡፡