ክታብል-ሙቀደስ (መጽሐፍ ቅዱስ) እንዲህ ይላል፡- “ከዚህ በኃላ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁ ሕልም ያልማሉ፤ ጎልማሶቻችሁ ራእይ ያያሉ” (ኢዩኤል 2፡28)፡፡
- • አላህ ልቦቻችንን ሊመረምርና ሎሎችን ለመርዳት ሕልሞችን ይጠቀማል፡፡ አንዳንዴ በልባችን ውስጥ እያሉ እኛ ችላ ያልናቸውን ነገሮችን እንድናይ ሕልሞቻችን ያነሳሱናል፡፡
- • አላህ ጆሮዎቻችንን ለመክፈት ሕልሞችን ይጠቀማል፡፡ የአላህን ድምጽ ለመስማት ሁል ጊዜ ዝግጁ አይደለንም፤ ምክንያቱም ከሥራ ብዛትና ከባተሌነታችን የተነሣ ጆሮዎቻችንን ዘግተን እርሱን ለመስማት የሚያስፈልገውን ጊዜ አንወስድም፡፡ አላህ ልቦቻችን እርሱን እንዳይሰሙ እንዲደነድኑ ያደረጉትን መጋረጃዎች በማለፍ በሕልም ይናገረናል፡፡
- • አላህ ትዕዛዝ ለመስጠት ሕልሞችን ይጠቀማል፡፡ በህልሞቻችን በመጠቀም አላህ ከስህተታችና ከያዝነው መጥፎ አቅጣጫ እንድንመለስ ያዘናል፤ በመልካም መንገድ ላይ እንድንጓዝም ይመክረናል፡፡ በእነዚህ ትዕዛዞች ብዙ ነገሮችን መማር እንችላለን፡፡
- • የግል የራስ መከላከል ግድግዳዎችን ለማፍረስ አላህ ህልሞችን ይጠቀማል፡፡ ሕልሞችን በመጠቀም አላህ ራስን የመከላከል ግድግዳችንን፣ ስለጥንካሬያችንና ስለድካማችን ያሉንን የተሳሳቱ አመለካከቶቻችንን ጥሶ ያልፋል፡፡ ሕልሞች የጉዳዮቻችን እምብርት ድረስ ዘልቀው ይገባሉ፡፡
እንደዚሁም፤ የሚከተሉትን ለማድረግ አላህ በህልም ይናገራል፡-
- • ከክፉ ለመግታት - ዘፍጥረት 20፡3
- • ፈቃዱን ለመግለጽ - ዘፍጥረት 28፡11-22፤ 37፡5-10
- • ወደፊት ስለሚሆኑ ክስተቶች የመንግስት ባለሥልጣናትንና የዓለም መሪዎችን ለማስጠንቀቅ - ዘፍጥረት 41፡1-8
- • ለነብያቱ መገለጥ ለመስጠት - ዘዑልቁ 12፡6
- • ሕዝቡን ለማደፋፈር - መሳፍንት 7፡13-15
- • የሙኢምንን ልመናዎችና ጸሎቶችን ለመመለስ - 1ነገስት 3፡5-15
- • ሊያዘን - ማቴዎስ 1፡20
- • የተሳሳቱ ውሳኔዎችን ከመወሰን እንዲቆጠቡ ሕዝቡን ለማስጠንቀቅ - ማቴ 27፡17-19