በጨለማ ውስጥ ነበር የምኖረው፡፡ ወዴት መሄድ እንዳለብኝ አላውቅም ነበር፡፡ ያለሁበትን አላውቅም ነበር፡፡ በየምሽቱ በግራ መጋባት ተሞልቼ ወደ አልጋ እሄድና እያለቀስኩ አንቀላፋለሁ፡፡
የምኖረው ክርስትና በማይታወቅበት በሰሜን ምዕራብ አፍሪካ ሃገር ውስጥ ነው፡፡ ወላጆቼ ሲፋቱ እናቴ ከክርስቲያን ሚሲዮናውያን ጋር ወዳጅነት ፈጠረች፡፡ ከእርሷና ከእኔ ጋር መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጀመሩ፡፡ ሙስሊሙ አባቴ ይሄን ነገር ሲያውቅ ከእናቴ ነጥሎኝ ከእርሱ ጋር እንድኖር አደረገኝ፡፡ አዲሱን ኑሮዬን ከመጥላቴ የተነሳ ድቅድቅ ጨለማ የሚመስል ድብርት ውስጥ ገባሁ፡፡
One night, my mother had a dream about living near a church. አንድ ቀን እናቴ ከቤተክርሲቲያን አጠገብ እንደምትኖር ሕልም አለመች፡፡ ከአላህ የመጣ መልዕክት መሆኑን በመገንዘብ በሕልሟ ያየችውን ቤተክርስቲያን የሚመስል ማፈላለግ ጀመረች፡፡ ስታገኘው በአቅራቢያው ለመኖር ሰፈር ቀየረች፡፡ እዛ እያለች፣ አላህ ብቻ ሊያዘጋጅ በሚችል መልኩ ወንጌላዊ ኢብራሂምን አገኘችና ከእርሱ ጋር መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ጀመረች፡፡ እናቴ ልቧ በመንፈስ ቅዱስ ተነካ፤ ከዚያም በኢሳ አል-መሲህ አመነች፡፡
ከዚያ በኋላ እናቴ ሌላ ሕልም አለመች፡፡ በዚህ ጊዜ ለጎረበቷ ዳቦ ስለመስጠት ነበር ሕልሙ፡፡ አዲሱን እምነቷን ለሌሎች እንድታጋራ የቀረበላት ጥሪ መሆኑን ተረዳች፡፡ ለመጠመቅም ወሰነች፡፡ ከጎሳዋ መካከል በኢሳ አል-መሲህ ለማመን የመጀመሪያ ሰው ሆነች፡፡
በዚህ ጊዜ እኔ ከአባቴ ጋር እኖር ነበር፤ ድብርቴም እያየለ መጣ፡፡ እናቴን ስጎበኛት የታመምኩ እመስላት ነበር፤ ምክንያቱም ሰውነቴ ገርጥቶ እየከሳሁ እሄድ ነበር፡፡ ሁል ጊዜ አትጨነቂ እላት ነበር፡፡ ትጸልይልኝ ነበር፤ ነገር ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንድርቅ ሰይጣን የሚቻለውን ሁሉ ያደርግ ነበር፡፡
አንድ ቀን ልቋቋመው ከምችለው በላይ ሆነብኝ፡፡ ራሴን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ ድረስ እያለቀስኩ ከዚህ በኋላ ከአባቴ ጋር መኖር እንደማልችል ለእናቴ ነገርኳት፡፡ ብቸኝነት ተሰማኝ፤ የተጣልኩም መሰለኝ፡፡ አጽናናችኝና አብረን ጸለይን፡፡ እርሷ ከክፍሌ ከወጣች በኋላ ለብቻዬ ጸለይኩኝ፡፡ እንዲደርስልኝና ይህን ሁሉ ሐዘንና ግራ መጋባት ከላዬ ላይ እንዲያነሳልኝ ጌታን ለመንኩት፡፡
በደስታ ተሞላሁ፡፡ አላህ ተዓምር አደረገ!
በሚቀጥለው ቀን በቀለለ መንፈስና ፈገግ ባለ ፊት ነቃሁ፡፡ ሊገለጽ በማይችል ፍስሐ ተሞላሁ፡፡ አላህ ሕያው መሆኑንና ጸሎቶቻችንን የሚመልስ አምላክ መሆኑን ተረዳሁ፡፡ እነዚህ ልምምዶች ከኢብራሂም ጋር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንድጀምር አደፋፈሩኝ፡፡ ተዓምራዊ በሆነ መልኩ አባቴ ከእናቴ ጋር ለአራት ወራት እንድቆይ ፈቀደልኝ፡፡
በመጨረሻም ከአባቴ ጋር ለመኖር ተመልሼ ሄድኩኝ፡፡ ነገር ግን ዒሳ ከእኔ ጋር መሆኑን ስላወቅሁ አዲስ መተማመንና ሰላም ነበረኝ፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ በጎረቤት አገር ተጠመቅሁ፡፡ በዒሳ አል-መሲሕ በኩል የትልቅ ቤተሰብ (ኡመት) አካል መሆኔን ተረዳሁ፡፡ እኔና እናቴ ጌታ አሁንም በሕይወታችን ሊሰራ ያሰበውን ስራ ገና እንዳልጨረሰ እናውቃለን፡፡