የአቤድ አል-መሲህ ታሪክ

ተወልጄ ያደኩት በመካከለኛው ምሥራቅ እምብርት ውስጥ ነው፡፡ እግዝአብሔር የለም ብዬ በማመን ነው ያደኩት፡፡ ነገር ግን በአሥራ እድሜዎቼ ውስጥ ወግ አጥባቂ ሙስሊም ሆንኩኝ፡፡ ክርስቲያኖችንና እነርሱ የሚያምኑበትን ክርስቶስን እንድጠላ ተምሬ ነው ያደኩት፡፡ እነዚህ ከሃዲዎች ያልነጹና ውሸት የሚያምኑ ናቸው፡፡ እንዲያውም ቀጥተኛይቱን መንገድ፣ እውነተኛውን የአላህን እምነት የማይከተሉትን ሰዎች ሁሉ ቤተሰቦቼንም ጨምሮ እስከ መጥላት ድረስ ደረስኩ፡፡ በዚህ በመከራና በጥላቻ ጊዜ የ17 ዓመት ጎረምሳ እያለሁ ለአጠቃላይ ፈተና ለመዘጋጀት እያጠናሁ እያለሁ ነጭ የለበሰ ሰው ከፊቴ ቆሞ አየሁት፡፡ እጁን ትክሻዬ ላይ በማድረግ “እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ” አለኝ፡፡ “እንድትከተለኝና እንድታገለግለኝ እፈልጋለሁ፡፡ ብዙ ችግሮች ይገጥሙሃል፤ ነገር ግን እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፡፡ በእኔ ድል ታገኛለህ፡፡ አንተ የእኔ ነህ” አለኝ፡፡ በዚያች ቅጽበት ከዚህ በፊት ያልተለማመድኩትን ሰላም አገኘሁ፡፡ እራሱ ሰላም በሆነው አልዎት ውስጥ ነበርኩ፡፡

እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ ያለኝ ማነው? አላወቅሁም፡፡ ስለዚህ መልስ ለማግኘት ፍለጋ ጀመርኩ፡፡ አንድ ክርስቲያን ክርስቶስ ነው በወንጌል ውስጥ እንዲህ ብሎ ራሱን የሚጠራው አለኝ፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲሰጠኝ ጠየቅሁት፡፡ በዚያች ሌሊት ዮሐንስ 14፡6ን እስካገኘሁ ድረስ አዲስ ኪዳንን ሁለት ጊዜ አነበብኩ፡፡

ከሁለት ቀን በኋላ አላህ ሕልም ላከልኝ፡፡ በሕልሜም ከሰዎች ጋር ጫካ ውስጥ ስንሄድ አየሁ፡፡ አንድ ጨለማ ቦታ ስንደርስ አንዳንዶቹ ጉዞውን መቀጠል ፈሩ፡፡ እኔ ግን እቀጥላለሁ አልኩኝ፡፡ ይህ አራት ጊዜ ተደጋገመ፤ በመጨረሻም ብቻዬን መራመድ ቀጠልኩ፡፡ መንገዱ ትንሽ፣ አሮጌና አንዲት ሻማ የሚበራባት ቤት ደርሶ አበቃ፡፡ ወደ ቤቱ ስገባ መብራቱ ጠፋ፡፡ ተንበርክኬ አይኖቼን በመጨፈን “ለምን” ብዬ ጠየቅሁኝ፡፡

በድንገት ትክሻዬ ላይ እጅ ሲያርፍ ተሰማኝ፡፡ አይኖቼን ከፍቼ ተነስቼ ቆምኩኝ፡፡ አሮጌው ቤት አዲስ ሆኖ በብርሃን ተሞልቶ አገኘሁት፡፡ ከዚህ በፊት ያየሁት ሰው ከጎኔ ቆሞ ነበር፡፡ “ሂድ፣ አትፍራ፣ እኔ ሁል ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ” አለኝ፡፡

አላህ ሕይወቴን የነካው በዚህ መልኩ ነበር፡፡ አሁንም በየቀኑ ከትክሻዬ ላይ እጁ ይሰማኛል፡፡ ለሕይወቴ አለማና እቅድ እንዳለው አውቃለሁ፡፡ የእርሱን ዱካና አቅጣጫ እየተከተልኩ ላገለግለው የምችለውን ሁሉ እያደረኩ ነኝ፡፡

ልባችንንና አህምሮአችንን ከጥላቻ ሊያነጻ የሚችለው ክርስቶስ ብቻ ነዉ፡፡ እርሱ ብቻ ነው የመንፈስ ፍሬ በሆኑ በፍቅር፣ በደስታ፣ በትዕግስት፣ በደግነት፣ በበጎነት፣ በእምነት፣ በየዉሃትና ራስን በመግዘት (ገላትያ 5፡22-23) ሊሞላን የሚችለው፡፡ ክርስቶስን እንዲከተሉና ሕይወትዎትን እንዲቀይርልዎት እንዲፈቅዱለት እጋብዝዎታለሁ፡፡ ወደ አብ የሚያደርስ መንገድ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ “ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ ‘መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም’” (ዮሐንስ 14፡6)፡፡

More Stories
People of the Book (Ahl Al-Kitab)
አማርኛ