የሁሴን ታሪክ

ሁሴን እባላለሁ፡፡ ከመካከለኛው ምስራቅ የመጣሁ ስደተኛ ነኝ፡፡ ከጦርነት ለመሸሽ ብዬ ነው አገሬን ለቅቄ የወጣሁት፡፡ ብዙ የቤተሰብ አባላትና ጓደኞቼን አጥቼአለሁ፡፡ በመንግስት ወይም በአክራሪ ቡድኖች ልገደል ስለምችል ወደ አገሬ መመለስ አልችልም፡፡ 

አንድ ቀን ለሕልሜ ትርጉም ለማግኘትና ይህ ሁሉ ግጭትና ግራ መጋባት ለምን እንደሚከሰት ለመረዳት በኢንተርኔት ላይ መልስ መፈለግ ጀመርኩ፡፡ በፈተና ውስጥ ነበርኩ፡፡ ለምንድነው ይህን ሁሉ የምሰቃየሁ፤ ለምንስ የምወዳቸውን ሰዎች አጣሁ? ለምንድነው በሕልሜ ነጭ የለበሰ ሰው የሚታየኝ? ማነው እርሱ? ከእኔ ምን ይፈልጋል? በኢንተርኔት ላይ እየፈለግሁ እያለሁ አንድ ነገር ቆም ብዬ የሆነ የኢንተርኔት ገጽ እንድመለከት ገፋፋኝ፡፡ “የኢሳ ሕልሞች” የሚል ነበር፡፡ ከዚህ በፊት ይህን በይነ-መረብ ገጽ አይቼ አላውቅም፡፡ ምን አገኝ ይሆን? ጥያቄዎቼን ይመልሱ ይሆን? ገጹን እንድመለከት የሚገፋፋኝን ኃይል መቋቋም አልቻልኩም፡፡ ደግሞም አረብኛንም ጨምሮ ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች መተርጎሙ ደስ አሰኘኝ፡፡ እየከፈትኩ ከማንበብ ማቆም አልቻልኩም፡፡ ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም፡፡ በጣም ሳቢ ነበር፡፡

የስልክ ቁጥር እዛው ላይ ስላገኘሁ መልዕክት ላኩኝ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ምላሽ ሲመጣልኝ ገረመኝ፡፡ ሰዉዬው ተግባቢ ነበር፡፡ ጥያቄዎች ቢኖሩኝ እንድጽፍለት ጋበዘኝ፡፡ ያ ምልልስ ለጥያቄዎቼ መልስ እንዳገኝ በር ከፈተልኝ፡፡ 

በመጀመሪያ የሕልሜን ትርጉም ጠየኩኝ፡፡ ሰውዬው ጥያቄዎቼን በብቃት ይመልስ ነበር፡፡ የሰጠኝ መልሶች ትክክልና ተከራክሬ ማጣጣል የማልችላቸው ነበሩ፡፡

ከዚያም ሌሎች ጥያቄዎችን መጠየቅ ጀመርኩኝ፡፡ በደንብ ተረድቶኝ ጥያቄዎቼን በፍቅርና በትዕግስት ይመልስልኝ ነበር፡፡ እነዚያን ጥያቄዎች የኃይማኖታችን መሪዎችን ብጠይቅ ይገስጹኝ ነበር፤ እንዲያውም ንስሃ መግባት የሚገባኝ አላማኝ ያደርጉኝ ነበር፡፡ ሰውዬውን እገዳደረው ነበር፤ እርሱ ግን ተረጋግቶ ይመልስልኝ ነበር፤ ስለሚያምነውም ነገር እርግጠኛ ነበር፡፡ ክታብ አል-ሙቀደስን (መጽሐፍ ቅዱስን) እና ቁርአንን አብረን ማጥናት ጀመርን፡፡ ሁለቱንም መጻሕፍት ያዉቅ ነበር፡፡ ሁሉንም ነገር ተነጋገርን፡፡ አርዕስቶቹ - መጽሐፍ ቅዱስ የተበረዘ መሆን አለመሆኑን፣ የኢሳ ማንነት፤ ስላሴ፣ የኢሳ በመስቀል ላይ መሞት፣ የቤተሰብ ጉዳዮች፣ የመጽሐፍ ቅዱስና የቁርአን አጻጻፍ (መንፈሳዊ አሰጣጥ)፣ የሐዲዝ እውነተኝነት፣ ወ.ዘ.ተ፡፡ ነገሮችን ለየት ባለ መልኩ እንዳይ አደረገኝ፡፡ ከብዙ ወራት ምልልስና ጥናት በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ የአላህ ቃል መሆኑንና አለመበረዙን ተቀበልኩ፡፡ ነገር ግን ኢሳ አምላክ መሆኑን አልተቀበልኩም ነበር፡፡ ልክ ቁርአን እንደገለጸው ነበር ኢሳን እመለከት የነበረው፡ - “[እርሱ ከአላህ] ባለሟሎች አንዱ ነው” (ሱረቱ አል-ኢምራን 3፡45)፡፡

አንድ ቀን፤ ስለ ኢየሱስ ብዙ ከተወያየን በኋላ እንዲህ አልኩት፡- “አዝናለሁ፤ አንተ እያልከኝ ያለውን ነገር ለማመን አልችልም፡፡” ከዚያም አንድ እንግዳ ነገር አደረገ፡፡ አላህ ማንነቱን በሙላት እንዲገልጥልኝ ጸለየ፡፡ “አላህ ሁሌም እውነትን ለሚፈልጉት ይገልጥላቸዋል” አለኝ፡፡

በሚቀጥለው ንጋት አካባቢ ሕልም አየሁ፡፡ በሕልሜም ነጭ የለበሰ ሰው እያነጋገረኝ እንዲህ ሲል ጠየቀኝ፡- “ስለማንነቴ ለምን ትጠራጠራለህ?”

እኔም “አንተ ማነህ?” አልኩት፡፡

እርሱም “እኔ መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወትም ነኝ፡፡ ቀጥተኛው መንገድ እኔ ነኝ፡፡ ጓደኛህ የሚልህን ስማው፡፡ እውነቱን ነው እየነገረህ ያለው” ብሎ መለሰልኝ፡፡

በዚያ ጠዋት መግለጥ በማልችል በሚያስገርም ሰላም፣ ደስታና ፍስሐ ተሞልቼ ነቃሁ፡፡ ከዚያም ጓደኛዬን ደውዬ ነገርኩት፡፡ “የሱስን በሕልሜ አየሁት፤ እርሱ አምላኬና አዳኜ እንደሆነ አምናለሁ!” አልኩት፡፡ ጓደኛዬ በጣም ደስ አለው፤ በስልክም ጸሎት አደረግን፤ ወደ ሙሉ እውነት ስለመራኝም ኢሳን አመሰገነው፡፡ ሕይወቴን ሙሉ በሙሉ ለእርሱ እንዳስረክብ አደፋፈረኝ፡፡ በዚያ የጋራ ጸሎት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢሳ ስም ጸለይኩኝ፡፡

አላህ ወደ በይነ-መረቡ እንዴት እንደመራኝ፣ ሕልሞቼን እንድረዳና ጥያቄዎቼን እንዴት እንደመለሰ ገባኝ፡፡ ለወራት በዘለቀውና ብዙ ትምህርት ባገኘሁበት ጥናት እንዴት እንደመራኝ ገባኝ፡፡ እውነቱንም በሕልም በማየው ነጭ የለበሰ ሰው አማካኝነት በልቤ እንዳተመልኝ ገባኝ፡፡ አዳኜንና ጌታዬን በማወቅ ሂደት ላይ አሁንም እያደኩኝ ነው፡፡ እባክዎትን በጸሎትዎት ያስቡኝ፡፡

More Stories
Can the Bible be Distorted?
አማርኛ