“When Allah showed them to you in your dream as few; and if He had shown them to you as many, you [believers] would have lost courage and would have disputed in the matter [of whether to fight], but Allah saved [you from that]. Indeed, He is Knowing of that within the breasts.” (Al-Anfal 8: 43)
“አቢ ሰይድ አል-ከሁዳሪ ነቢዩ እንዲህ ሲሉ መስማታቸውን ተናግረዋል፡ - ከእናንተ መካከል ማንም ደስ የሚያሰኘው ሕልም ካየ ሕልሙ ከአላህ ነው ማለት ነው፤ ስለዚህ አላህን ማመስገን አለበት፣ ለሌሎችም ማውሳት አለበት፡፡ ነገር ግን ሌላ ነገር ካየ - ማለትም የማያስደስተው ሕልም - እሱ ከሰይጣን የተላከ ሕልም ነው፡፡ ከክፉው ለማምለጥ ከአላህ ከለላ መጠየቅ አለበት፤ ስለማይጎዳው ለማንም መንገር የለበትም፡፡” .”(Mokhtaser Sahih Al-Bukhari, book of the interpretation of dreams, p. 1165).
አስቀድመን ትርጉሞቹን እንመልከት፡፡
ሕልም፡- “ሕልም በእንቅልፍ ጊዜ በሰው አህምሮ የሚዘዋወሩ የሃሳቦች፣ የምስሎችና የስሜቶች ፍሰት ነው” (Webster’s New World Dictionary).
ራእይ፡- “ከተለመደው እይታ ውጭ የታየ፤ በሕልም፣ በመገለጥ ወ.ዘ.ተ ወይም ለነቢያት እንደሚገለጥ አይነት ከአምላክ የሚገለጥ ነገር” (Webster’s New World Dictionary).
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ሕልምና ራእይ 106 ጊዜ ተወስቷል፡፡ ነቢዩ ዳንኤልና ሐዋርያው ጳውሎስ ከሌሎች ሰዎች የበለጠ አይተዋል፡፡ - ነቢዩ ዳንኤል 26 ሲያይ ሐዋርያው ጳዉሎስ ደግሞ 6 አይቷል፡፡
“እግዚአብሔር ይላል። በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ፤ ደግሞም በዚያች ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ ትንቢትም ይናገራሉ” (ቅዱስ ኢንጂል የሐዋርያት ሥራ 2፡17-18)።
አላህ ትዕዛዛትን ለማስተላለፍ ህልሞችንና ራዕዮችን ይጠቀማል፡፡ በሕልሞቻችን አላህ ስህተቶቻችንን እና የተሳሳተ አቅጣጫችንን ይጠቁመንና እንዴት ወደፊት መጓዝ እንደሚገባን ያዘናል፡፡ “ሰው ባያስተውለውም፣ እግዚአብሔር በተለያየ መንገድ ይናገራል፤ ሰዎች በአልጋቸው ላይ ተኝተው ሳሉ፣ ከባድ እንቅልፍ ሲወድቅባቸው፣ በሕልም፣ በሌሊትም ራእይ ይናገራል፡፡ በጆሯቸው ይናገራል፤ በማስጠንቀቂያም ያስደነግጣቸዋል፤ ሰውን ከክፉ ሥራው ይመልሳል፤ ከትዕቢት ይጠብቃል፤ ነፍሱን ከጉድጓድ፤ ሕይወቱንም ከሰይፍ ጥፋት ያድናል” (ተውራት አዩብ 33፡14-18)::
ስለዚህ፣ ከላይ በተጠቀሱት ጥቅሶች መሠረት አላህ በሕልሞች የሚናገረው፡-
1. ክፉ ከመስራት ሰዎችን ለመመለስ
- • የንጉስ አቢሜሌክ ሕልም (ዘፍጥረት 20፡1-7)
- • የሳኦል ራዕይ (የሐዋርያት ሥራ 9፡1-9)
- • ላባን ያዕቆብን እንዳይጎዳው ማስጠንቀቂያ ደረሰው (ዘፍጥረት 31፡29)
2. ሰዎችን ከትዕቢት ለመጠበቅ
- • የናቡከድናፆር ሕልም (ዳንኤል 4፡10-18)
3. ሰዎችን በትክክለኛ አቅጣጫ ለመምራት
- • ለቆርነሊዎስና ለጴጥሮስ የተሰጡ ሁለቱ ሕልሞች (የሐዋርያት ሥራ 10፡1-8)
4. ሰዎችን ከሞት ለመጠበቅ
- • ሊመጣ የነበረውን ረሃብ ፈርዖን በሕልም ማየቱ (ዘፍጥረት 41፡14-24)
- • የየሱስን ሕይወት ያዳነው የሰብአ ሰገሎቹና የዮሴፍ ሕልሞች (ማቴዎስ 2፡1-18)
አላህ ከአለማወቅ የሚነሱትን የእምቢታ ግድግዳዎቻችንን ለማፍረስ በሕልም ይጠቀማል፡፡ ከአላህ የሚላኩ ሕልሞች ቀጥታ ወደ ጉዳዩ እምብርት የሚደርሱ ሲሆኑ እውነቱን በግልጽ እንድንረዳ ያደርጉናል፡፡ አላህን በአዲስ መንገድ መመልከት መቻል ትልቅ እድል ነው፡፡
ሁሉም ሕልሞች ከአላህ የሚላኩ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ሕልሞች ከሦስት ምንጮች ሊመነጩ ይችላሉ፡- (1) ከአላህ፤ (2) ከተፈጥሮአዊ መንስኤዎች፤ እና (3) ከሰይጣን፡፡ ሕልም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይቃረን ከሆነ ከአላህ የተላከ ሊሆን ይችላል፡፡
አላህ ዛሬም በህልምና በራእይ ይናገራል፡፡ የእነዚህን ሕልሞች ትክክለኛ ትርጉም ስንረዳ እንደ ፈቃዱ መኖር እንችላለን፡፡ አሁኑኑ እየተናገረዎት ሊሆን ይችላል፡፡ ምላሽዎት ምንድነው? የህልምዎትን ምንነትና ዓላማ ለመረዳት መጣር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እኛ ደግሞ አላህ የሰጠዎትን ህልም እንዲረዱ ልንደግፍዎት ዝግጁ ነን፡፡
ቁርዓን ስለ ሕልም ይናገራል፡-
- • ቁርዓን 8:43
- • ቁርዓን 12:4-6, 36-37, 43-46, 100-101
- • ቁርዓን 17:60
- • ቁርዓን 37:102-105
ብሉይ ኪዳን ስለ ሕልም ይናገራል፡-
- ዘፍጥረት 20:3
- • ዘፍጥረት 28:11-22
- • ዘፍጥረት 31:10-13
- • ዘፍጥረት 37:1-10
- • ዘፍጥረት 40:9-19
- • ዘፍጥረት 41
- • መሳፍንት 7:13-15
- • 1ኛ ነገስት 3:5–15
- • ዳንኤል 2
- • ዳንኤል 4
- • ዳንኤል 7
አዲስ ኪዳን ስለ ሕልም ይናገራል፡-
- • ማቴዎስ 1:18–2:23
- • ማቴዎስ 27:19