“ስትጸልዩ እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ እነርሱ ለሰዎች ለመታየት ሲሉ በየምኵራቡና በየመንገዱ ማእዘን ላይ ቆመው መጸለይ ይወድዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ሙሉ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ክፍልህ ግባ፤ በሩንም ዘግተህ በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተደረገውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል። ስትጸልዩ፣ ከንቱ ቃላት በመደጋገም ጸሎታቸው የሚሰማላቸው እንደሚመስላቸው አሕዛብ ነገራችሁን አታስረዝሙ። እነርሱን አትምሰሏቸው፤ አባታችሁ ከመለመናችሁ በፊት ምን እንደሚያስፈልጋችሁ ያውቃልና” (ማቴዎስ 6፡5-8)።
ኢሳ ደረሳዎቹን ጸሎት ያስተማረው እንዴት ነበር?
በማቴዎስ 6፡9-13 ላይ ኢሳ ወደ አላህ እንዴት መጸለይ እንዳለብን ያስተምረናል፡፡ ይህ ጸሎት በግል አላህን የምንለምነውን ዱኣ አይወክልም፡፡ መደጋገም ያለበት ጽሑፍም አይደለም፡፡ ይልቁንስ የአላህን ፈቃድ ለማወቅና ለሕይወታችን ምሪት ለማግኘት የምንጸልየው ጸሎት ነው፡፡ መልዕክቱ ከቃላት ድርደራ የበለጠ የጠለቀ ትርጉም አለው፡፡
““ስትጸልዩ እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ እነርሱ ለሰዎች ለመታየት ሲሉ በየምኵራቡና በየመንገዱ ማእዘን ላይ ቆመው መጸለይ ይወድዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ሙሉ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።
አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ክፍልህ ግባ፤ በሩንም ዘግተህ በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተደረገውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል። ስትጸልዩ፣ ከንቱ ቃላት በመደጋገም ጸሎታቸው የሚሰማላቸው እንደሚመስላቸው አሕዛብ ነገራችሁን አታስረዝሙ። እነርሱን አትምሰሏቸው፤ አባታችሁ ከመለመናችሁ በፊት ምን እንደሚያስፈልጋችሁ ያውቃልና”:
“እናንተ ግን እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፤
“ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤
ስምህ ይቀደስ፤
መንግሥትህ ትምጣ፤
ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች፣
እንዲሁ በምድር ትሁን።
የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን።
እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፣
ከክፉው አድነን እንጂ፤
መንግሥት፣ ኃይል፣ ክብርም
ለዘለዓለሙ ያንተ ነውና፤ አሜን
ወደ ፈተናም አታግባን
ከልብ ብንጠራው ኢሳ በእውነት ይሰማናል?
ከልጅነታችን ጀምረን ከሚያዳምጡን፣ ከሚመክሩንና ከሚወዱን ሰዎች ጋር የጠበቀ ጓደኝነጽ መመስረት እንፈልጋለን፡፡ ኢሳ አል-መሲህ ሁል ጊዜ ልንወዳጀው የምንፈልገው የልብ ወዳጃችን ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ እርሱ ከእኛ ጋር ያለው ግንኙነት ቋሚ ነው፡፡ እኛ እርሱን ካለማወቃችን የተነሳና ከእርሱ ከመራቃችን የተነሳ ግንኙነታችን የላላ ሆነ፡፡ እርሱ ራሱ ግን ወደ እኔ የሚመጡትን ወደ ኋላ አልመልስም ብሏል፡፡
“አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ ወደ እኔ የሚመጣውንም ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም” (ኢንጂል ዮሐንስ 6፡37)፡፡
እነዚህ የኢሳ የራሱ ቃላት ናቸው፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው ማመን ብቻ ነው፤ ቀሪውን አላህ ይፈጽመዋል፡፡
አላህን በግል ደረጃ እንዴት ማወቅ እንችላለን?
ከፈጣሪያችን ጋር የግል ግንኙነት እንዲኖረን ከተፈለገ የኢሳን ማንነት መረዳት አለብን፡፡ ኢሳ በቁርዓንም ሆነ በኪታብ አል-ሙቀደስ (መጽሐፍ ቅዱስ) ውሰጥ ተወስቷል፡፡ የተለያዩ መጽሐፎች ቢሆኑም ሁለቱም ስለ ኢሳ ይገልጻሉ፡፡ ስለዚህ ኢሳን ለመረዳት መጽሐፍ ቅዱስን ብናጠና ስለ አላህ የተሻለ መረዳት እናገኛለን፡፡
በግል ደረጃ አላህን ለመረዳት የተሻለው መንገድ የኢሳ አል-መሲህን ሕይወት ማጥናት ነው፡፡ ይህን ስናደርግ በምን በምን መልኩ ሰው እንደሆነና በምን በምን መልኩ አምላክ እንደሆነ ልንረዳ እንችላለን፡፡
የኢሳ አል-መሲህን የሕይወት ታሪክ ለመረዳት ከፈለጉ “የዘመናት ምኞት” የሚለውን መጽሐፍ ያንብቡ፡፡
ከአላህ ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ጸሎት ወሳኝ ነው፡፡
ከአላህ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ልክ ከቤተሰቦቻችንና ከጓደኞቻችን ጋር ጊዜ እንደምናሳልፈው ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን እንዘነጋለን፡፡ በተጨማሪም፣ ከሁሉም በላይ ልንጠነቀቅለት የሚገባን ግንኙነት ነው፡፡ የሚደጋገም ጸሎት የምንደጋግምበት ጊዜ አይደለም፤ ይልቁንስ ለአላህ እኛነታችንን ሙሉ በሙሉ የምናስረክብበት የግል ዱኣ ነው፡፡
ጸሎት የምንፈልገውን ነገር የምንጠይቅበት ጊዜ ብቻ አይደለም፤ እንደዚሁም የሆነ ነገር ስንፈልግ ብቻ መጸለይ የለብንም፡፡ ኢሳ አል-መሲህ እንዲህ ብሎናል፡- “ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን እሹ፤ እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል” (ማቴዎስ 6፡33)።
ብዙ ጊዜ ስለችግሮቻችን ነው የምንጸልየው፡፡ ስለ አዲስ ስራ፣ ስለ ትዳር ጓደኛ፣ ስለ ፈውስ፣ ስለ ገንዘብ እርዳታ፣ ምናልባትም ስለ ውሻ ቡችላ እንጸልይ ይሆናል፡፡ ምንም ሆነ ምን፣ አንዳች ነገር ስንፈልግ ብቻ ወደ አላህ መሄድ ትክክል አይደለም፡፡ በመጀመሪያ ወደ እርሱ የምንሄደው እርሱን ፈልገን፣ አልዎቱንና ምሪቱን ፈልገን መሆን አለበት፤ ከዚያም ሁሉም ይጨመርልናል፡፡
አላህ ልባችንን ያዉቃል፤ ሁኔታችንን ይረዳል፡፡ ንስሐ ባንገባ (ባንቶብት) እንኳን ስህተት ስንሰራ ያዉቃል፡፡ ነገር ግን ከእርሱ ጋር ግንኙት ስንፈጥር ነው ነገሮች ሊሳኩልን የሚጀምሩት፡፡ አንዳንድ ጊዜ እኛ እንደምንፈልገው ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን እርሱ እንደፈቀደው ይሆናል፡፡
አስቡበት፡- ጓደኞችዎትና የቤተሰብዎት አባላት ሁል ጊዜ ወደ እርስዎ የሚመጡት የሆነ ነገር ከእርስዎ ለመለመን ቢሆን ምን ይሰማዎታል? ከእርስዎ ጋር የሚያወሩት ጊዜ ያ ብቻ ቢሆን ምን ይሰማዎታል? በዚያው ልክ ያስቡ - አላህ ከእርሱ ጋር ግንኙነት የመፍጠር ጉዳይ ሳይሆን ሁል ጊዜ ይሄን ስጠኝ፣ ያን ስጠኝ የሚል ልመና ቢቀርብለት ምን ይሰማዋል?