ንስሃ (ቶውበት)

“የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ትበረታላችሁ፤ እናንተ ግን ይህን አላደረጋችሁም” (ኢሳያስ 30፡15)፡፡

ሸይጧን አስገድዶ ክፉ ሊያሰራን እንደማይችል፣ ፈቃዳችንን ለእርሱ ካስረከብን በስተቀር (በአላህ ያለንን እምነት ካልጣልን በስተቀር) አህምሮአችንን መቆጣጠር እንደማይችል ማወቃችን አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን በእሽሩሩ የምንይዛቸው የሐጢያት ፍላጎቶቻችን ለሰይጣን መግቢያ ቀዳዳ ይከፍታሉ፡፡ የአላህ መለኮታዊ መስፈርቶችን አለማሟላታችን ሰይጣን ሊፈትነንና ሊያጠፋን የሚችልበት በር እንደ መክፈት ነው፡፡ እኛ ስንወድቅ ወይም ስንሸነፍ ሰይጣን ኢሳ አል-መሲህን ለመውቀስ ዕድል ያገኛል (የዘመናት ምኞት ምዕራፍ 13ን ያንብቡ)፡፡ (የዘመናት ምኞት ምዕራፍ 13ን ያንብቡ)፡፡

ኢሳ በማርቆስ 14፡38 ላይ “ትጉና ጸልዩ ወደ ፈተና እንዳትገቡ” ብሏል፡፡ ከወደቅንም በአላህ እርፍት ልናደርግ እንችላለን ምክንያቱም መንፈሱ (ሩህ አላህ) ሲመራን ነበር፤ ይሄው መንፈስ ነበር ኢሳ በዲያብሎስ እንዲፈተን ወደ በረሃ የመራው፡፡ አላህ እንድንፈተን ሲፈቅድ፣ ለራሳችን መልካም የሆነን ዓላማን ለመፈጸም ብሎ ነው፡፡

What Did Isa Mean by Finding Rest in Him?
በማቴዎስ 6 ውስጥ የተጻፈው የኢሳ እውቅ ቃላት በእርሱ እረፍት እንድናገኝ ይነግረናል፡፡ ግን ምን ማለቱ ነው? ወደ ኢሳ አል-መሲህ የበለጠ ስንጠጋ የበለጠ ባህሪውን እንመስላለን፡፡ ያኔ ሸክማችንም የቀለለ ይሆናል፤ ምክንያቱም ለአላህ የሚከብድ ነገር የለም፡፡ የሚገጥሙን ነገሮች ሁሉ ኢሳ አል-መሲህ በዚህ ምድር በነበረበት ጊዜ ከደረሰበት አይበልጡም፡፡ ከዚያም ኢሳ እንዲህ አለ፡- “እናንት ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ። ቀንበሬን ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ በልቤ የዋህና ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ፣ ሸክሜም ቀላል ነውና” (ማቴዎስ 11፡28-30)፡፡Come to me, all of you who are weary and carry heavy burdens, and I will give you rest. Take my yoke upon you. Let me teach you, because I am humble and gentle at heart, and you will find rest for your souls. For my yoke is easy to bear, and the burden I give you is light.”  Matthew 11:28-30

በዚህ ስፍራ ኢሳ አል-መሲህ ለሁላችንም ነው የሚናገረው፡፡ ሁላችንም ሸክም አለብን፤ እርሱ ደግሞ አስወግድላችኋለሁ ይለናል፡፡ ከሁሉም የሚበልጠው ሸክማችን የሐጢያት ሸክም ነው፡፡ ያለ ኢሳ አል-መሲህ እርዳታ ሐጢያታችንና ክብደቱ ያጠፋናል፡፡ በተውራት ውስጥ የሚገኘው የኢሳያስ መጽሐፍ በ53፡6 ላይ “ጌታ የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ” ይላል፡፡

በልቡ ላይ የሚሸከመን እርሱ ስለሆነ ኢሳ ሸክማችሁን በእኔ ላይ ጣሉ ይለናል፡፡ ኢሳ ድክመቶቻችንን፣ ጉድለታችንን፣ ፈተናችን ጉልበት የሚያገኝበትን ቦታንም ያውቃል፡፡ ምክንያቱም በሁሉም ነገር እንደ እኛው ተፈትኖ ነበርና፤ ነገር ግን በደል አልተገኘበትም፡፡ ኢሳ እንድናደርግ የሚጋብዘን ከእርሱ ፈቃድ ጋር እንድንስማማ ነው፡፡ ፈቃዱ ደግሞ የማይለካና በፍትረተ-ዓለም ላይ ከሚገኝ ነገር ሁሉ የሚበልጥ ነው፡፡ ከፍ ያለ፣ ጨዋና ከፍ የሚያደርግ ፈቃድ እንዲኖረን ይፈልጋል (በዚህ ጉዳይ ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት የዘመናት ምኞት የሚለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 34 ያንብቡ)፡፡

ንሰሃ (ቶውበት) ለምን አስፈለገ? Desire of Ages Chapter 34.

Why We Need Repentance?
“በስሜ የተጠራው ሕዝቤ ራሱን አዋርዶ ቢጸልይ፣ ፊቴን ቢፈልግና ከክፉ መንገዱ ቢመለስ፣ ከሰማይ እሰማዋለሁ፤ ኀጢአቱን ይቅር እላለሁ፤ ምድሩንም እፈውሳለሁ” (2ዜና 7፡14)።
በዚህ አያ (ጥቅስ) መሠረት አራት ነገሮች ያስፈልጉናል፡-
ትህትና
ክልብ አላህን መፈለግ
ከክፉ መንገድ መመለስ - ንስሓ መግባት (መቶውበት)
መጸለይ (ዱኣ ማድረግ)

“የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ትበረታላችሁ፤ እናንተ ግን ይህን አላደረጋችሁም” (ኢሳያስ 30፡15)፡፡

What is Repentance?”
The word repentance in the Bible means “change of mind” and “turning around”.

በክታብ አል-ሙቀደስ ውስጥ ንስሃ በምን መልኩ እንደተገለጸ እንመልከት፡-
ሀ. መዞር - የሐዋርያት ሥራ 9፡35
ለ. ንስሐ መግባት - የሐዋርያት ሥራ 2፡38፤ 3፡19፤ 8፡22፡፡
ሐ. መመለስ - 1ሳሙኤል 7፡3
መ. መለወጥ - የሐዋርያት ሥራ 15፡3
ስለዚህ ንስሃ (ቶውበት) ማለት - መለወጥ፣ መዞር፣ እና ሐጢያትን በተመለከተ የአህምሮና የሕይወት ለውጥ ማምጣት ማለት ነው፡፡

ንስሃ መግባታችንን የሚያሳዩ ማስረጃዎች ምን ምን ናቸው?
1. መንፈሳዊ ሐዘን - 2ቆሮንቶስ 7፡9-10
2. የሕይወት ተሃድሶ - ሉቃስ 3፡7-14
3. መመለስ - ሉቃስ 19፡1-10፡፡

ለንሰሃ መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎች፡-
1. የአላህ በጎነት - ሮሜ 2፡4
2. የአላህ ትዕግስት - 2ጴጥሮስ 3፡9
3. የበደለኝነት ስሜት - የሓዋርያት ሥራ 2፡37-38፡፡

More Stories
ሕልሞችና ራዕዮች
አማርኛ