ነጃት/ድነት

“እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ ድነት ቸል ብንል እንዴት ልናመልጥ እንችላለን? ይህ ድነት በመጀመሪያ በጌታ ተነገረ፤ ከእርሱ የሰሙትም ለእኛ አረጋገጡልን” (ዕብራውያን 2፡3)።

“What is the Message of Salvation; Redemption, and How Does One Receive Salvation and Redemption? “o just as sin ruled over all people and brought them to death, now God’s wonderful grace rules instead, giving us right standing with God and resulting in eternal life through Jesus Christ our Lord. (Romans 5:21 NLT)

የድነትና የመዋጀት መልዕክትን ይዞ ወደዚህ ዓለም የመጣው ኢሳ አል-መሲህ ብቻ ነው፡፡ ይህ የድነትና መዋጀት ተነሳሽነት አላህ ለሐጢያተኞች የሰዎች ልጆች ባሳየው ፍቅር ተገልጧል፡፡ የአላህ ፍትሐዊው ሕግ እንደሚናገረው “የሐጢአት ደመወዝ ሞት ነው” (ሮሜ 6፡23)፡፡ነገር ግን አላህ ሰው ሁሉ ሐጢያተኛ እንደሆነ ያውቃል፡፡ ከዚህ ነጻ የሆነ ሰው የለም፡፡ ከዚህ እውነታ ብቻ የተነሳ እኛ ሰዎችና አላህ አብረን መሆን አንችልም፡፡ ከዚህ የተነሳ ነው ኢሳ አል-መሲህ በእኛ በሐጢያተኞችና በአላህ መካከል አስታራቂ ሆኖ የመጣው፡፡ ለእኛ ብሎ ስለመጣ እርሱ ብቻ ነው ከአላህ ጋር ሊያስታርቀን የሚችለው፡፡ እርሱ ነው የሐጢያት መቀጮአችንን የከፈለው፡፡ በተጨማሪም፣ ኢሳ እኛ ልንቀበል ይገባን የነበረውን ቅጣት ተቀበለ፡፡ ከዚህ የተነሳ በመስቀል ላይ ሞቶ እኛን ዋጀን፡፡ ኢሳ እንዴት እንደዋጀን ሲገልጽ ሐዋሪያው ጳውሎስ ጎላ አድርጎ አብራርቷል፡፡ “የእግዚአብሔር ጠላቶች ሳለን በልጁ ሞት ከእርሱ ጋር ከታረቅን፣ ዕርቅን ካገኘን በኋላ፣ በሕይወቱማ መዳናችን እንዴት የላቀ አይሆንም! ይህ ብቻ አይደለም። ነገር ግን አሁን ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ ሐሤት እናደርጋለን” (ሮሜ 5፡10-11)።

ኢሳ ለአይሁድ፣ ለክርስቲያኖች፣ ወይም ለሙስሊሞች ብቻ አልመጣም፡፡ እርሱ ከአላህ ጋር ያስታረቀው አንድ ሕዝብ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንስ በሞቱ ሁላችንንም ከአላህ ጋር አስታረቀን፡፡ ሊፍረድብን ሳይሆን ሁላችንንም ሊያድነን ተላከ (ዮሐንስ 3፡17)፡፡ የአላህ ፍቅር ለሁሉም ሰው ነው፡፡ ሁላችንንም በቀጥተኛይቱ መንገድ እንድንመራ ይፈልጋል፡፡ , الصراط المستقيم, (ስራት አል-ሙስተቂም)፡፡). Allah’s love is for everyone, He desires each one of us to be led on the straight path, الصراط المستقيم, aṣ-Ṣirāṭ al-mustaqīm.

አሁን ኢሳ አል-መሲህ ከአላህ ጋር እንዳስታረቀን ካወቅን ዘንዳ፣ መዋጀትንና ድነቱን እንዴት ልንቀበል እንችላለን? 
ይህን ድነትና መዋጀት የምናገኘው በኢሳ አልመሲህ በማመን ነው፡፡ እርሱ መሲህና አዳኝ መሆኑን ማመን አለብን፡፡ የምናደርገው ነገር ቢኖር በእርሱ ማመን ነው፡፡ የተላከበትንም ምክንያት ማመን ነው፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው፣ ከሐጢያት መዳንና መዋጀት ለዓለም ሁሉ ነው፡፡ የሚፈለገው በክርስቶስ ማመን ብቻ ነው፡፡ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወድዷልና” (ዮሐንስ 3፡16)። ኢሳ አል-መሲህ ራሱ እንደዚህ ብሏል፡- “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሐንስ 14፡6)።. The words of Isa Al Massih Himself state the following: “I am the way, the truth, and the life. No one can come to the Father except through me.” (John 14:6).
“Who Did Isa Come to Save?”
የኢሳ አል-መሲህን ሕይወት ብዙም የማያዉቁ ሰዎችና ለምን እንደመጣ የማያውቁ ሰዎች ኢሳ ለጻድቃን የመጣ ይመስላቸዋል፡፡ በእነርሱ አመለካከት ኢሳ ጻድቃንን እንጂ ድሆችን፣ ጎስቋላ ሐጢያተኞችን ሊያድን አልመጣም፡፡ ይህ ከእውነቱ ተቃራኒ ነው፡፡ ኢሳ ልቦቻችንን ያውቃል፣ ልንድን የምንፈልግ ሰዎችን ያውቃል፤ እኛ የምናምን አላህ በቀጥተኛይቱ መንገድ እንዲመራን መለመን አያስፈልገንም፡፡ ሐጢያተኞች ብንሆንም፣ ልባችን የተሻለ ለማግኘት ይመኛል፡፡

ከ2000 ዓመታት በፊት ኢሳ አል-መሲህ ክፉ ሐጢያተኞችን ሊያድን ምን ያክል እንደሚፈልግ ሊያሳየን መጣ፡፡ እርሱና አላህ ባሉበት ቦታ አንድ ቀን እኛም እንድንሆን ሁለተኛ እድል ሰጠን፡፡ ከዳኑት ሰዎች መካከል አንዱ ማቴዎስ የተባለው ትሁት የኢሳ አልመሲህ ደረሳ (ደቀመዝሙር) የነበረ ሰው ነው፡፡ የቀድሞ ስሙ ሌዊ ነበር፡፡ ማቴዎስ ቀረጥ ሰብሳቢ ነበር፤ በዚያ ዘመን ቀረጥ ሰብሳቢ እንደ አጭበርባሪ ይታይ ነበር፡፡ እንደዚሁም በዚያ ዘመን የአይሁድን መሬት በጉልበት የያዙ ሮማውያንን ይደግፋሉ ይባላሉ፡፡ ቀረጥ ሰብሳቢዎች በሕዝብ ፊት የተጠሉና መንፈሳዊ ሰዎች እንዳልሆኑ ይቆጠሩ ነበር፡፡ ገንዘብ ከሕዝቡ መስረቅና በሌሎችም በማናቸውም መንገዶች ገንዘብ በማጋበስና ከሮማውያውያን ጋር በመተባበር ይታወቃሉ፡፡ “Follow Me.” “ተከተለኝ” አለው (ሉቃስ 5፡27)፡፡የሚታወቁት ፈሪሳውያን በኢሳ ደረሳዎች ላይ አጉረመረሙ፡፡ በመሆኑም “ለምን ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከሐጢያተኞች ጋር ትበላለህ?” ብለው ኢሳን ጠየቁት፡፡ “Why do you eat and drink with tax collectors and sinners?” to which Jesus said to the “Those who are well have no need of a physician, but those who are sick. I have not come to call the righteous, but sinners, to repentance.” عندما قال يسوع: "لقد جئت من أجل المرضى"، لم يكن يقصد الأشخاص الذين يعانون من أمراض جسدية، بل الأشخاص الذين يعانون من أمراض روحية وخسائر.

በተመሳሳይ መልኩ ኢሳ እንዳለው እርሱ የተላከው ወንጌልን ለድሆች ለመስበክ፣ ልባቸው የተሰበረውን ለመጠገን፣ ለምርኮኞች ነጻነትን ሊያውጅ፣ የአይነ-ስውሮችን አይን ለመክፈትና የተጨቆኑትን ነጻ ለማውጣት ነበር (ሉቃስ 4፡18)፡፡

ከዚህ በኋላ “መዳን እችላለሁ ወይ?” ብለው ወይንም “አላህ ይቅር ይለኛል?” ብለው ራስዎትን ሲጠይቁ አላህ ኢሳ አል-መሲህን የላከው ለሐጢያተኞች ሲሆን ንስሐ የመግባትና (የመቶበትና) የዘለዓለምን ሕይወት የማግኘት ሁለተኛ እድል እንደሰጣቸው ያስታውሱ፡፡ እርስዎም በዚህ ውስጥ እንደሚጠቃለሉ ያስታውሱ፡፡ 

አላህ ይወደናል፤ ሁላችንም ድነን ከእርሱ ከፈጣሪያችን ጋር እንድንሆን ይፈልጋል፡፡ ይሁን እንጂ እንድንወደውና እንድንታዘዘው አያስገድደንም፡፡ በጣም እኛን ከማክበሩና ከመውደዱ የተነሳ የምርጫ ነጻነት ሰጥቶናል፡፡ ልክ እንደ ጠፋው በግ ምሳሌ ኢሳ እርሱ ሐጢያተኞችን ይቅር ማለቱን የተቃወሙ ሰዎችን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው (ሉቃስ 15ን ይመልከቱ)፡፡ መቶ በጎች ያሉት ሰው አንዱ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በሜዳ ላይ ትቶ የጠፋውን ፍለጋ ይሄዳል አለ፡፡ እርሱም ስለእኛ እንደዚህ ይሰማዋል፡፡

ሐጢያተኞችን የምንወደው ክብርን በማሳየትና ለሕይወታችን ዋጋ የምሰጠውን ያክል ለሕይወታቸውም ዋጋ በመስጠት ነው (1ጴጥሮስ 2፡17)፡፡ እንደዚሁም ለእነርሱ በመጸለይና ከእነርሱ ጋር በመጸለይ (1ጢሞቴዎስ 2፡1) እና ስለ ክርስቶስ ለእነርሱ በመመስከር ፍቅራችንን እናሳያቸዋለን፡፡

See John 15.
ነቢዩ ኢብራሂም ለተለየ ተልዕኮ እንደተመረጠ መጽሐፍ ቅዱስም (ክታብ አል-ሙቀደስ) ሆነ ቁርዓን ይመሰክራሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “አገርህን፣ ወገንህንና የአባትህን ቤት ትተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ። “ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ፤ ደግሞም እባርክሃለሁ፤ ስምህን ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎች በረከት ትሆናለህ። የሚባርኩህን እባርካለሁ፤ የሚረግሙህን እረግማለሁ፤ በምድር የሚኖሩ ሕዝቦች፣ በአንተ አማካይነት ይባረካሉ” (ዘፍጥረት 12፡1-3):: በቁርዓን ውስጥም ተመሳሳይ ተስፋ ተሰጥቶታል፡፡ “እኔ ለሰዎች መሪ አድራጊህ ነኝ” (ሱረቱ አል-በቀራህ 2፡124)፡፡

ሁሉም ሙስሊሞች የኢድ አል አድሃ በዓልን ያከብራሉ፡፡ ይህ በዓል የሚከበረው ነቢዩ ኢብራሂም ለአላህ ያቀረበውን መስዋዕት ለማስታወስ ነው፡፡ ቁርዓን እንዲህ ይላል፡- ጌታዩ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡ ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡ ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ” (አል-ሷፋት 37፡100-102)፡፡

ሙስሊሞች ይህ ልጅ ይስሐቅ ሳይሆን እስማኤል ነው ይላሉ፡፡ ቁርዓን ግን ልጁ ይስሐቅ ይሁን እስማኤል ይሁን ግልጽ አድርጎ አልተናገረም፡፡ ልጁን እንዲሰዋ በመጠየቅ አላህ ነቢዩን ፈተነው፡፡ “ይህ እርሱ ግልጽ ፈተና ነው፡፡ በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተበዠነው” (አል-ሷፋት 37፡106-107)፡፡

ሙስሊም ፈሳሪዎች አብዛኛውን ጊዜ ይህ “ታላቅ ዕርድ (መስዋዕት)” አላህ በኢብራሂም ልጅ ፋንታ ያቀረበው የመስዋዕት በግን የሚወክል ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን በግ ከኢብራሂም ልጅ ጋር ሲነጻጸር በእርግጥ ታላቅ መስዋዕት ሊሆን ይችላል? ስለዚህ “ታላቁ ዕርድ (መስዋዕት)” ሌላ መስዋዕትን የሚወክል መሆን አለበት፡፡ ይህ ጥያቄ ያስነሳል፡፡ አላህ ወደፊት ሊመጣ ስለነበረው ታላቅ መስዋዕት እየተናገረ ይሆንን?

በእርግጥ ቁርዓን በዚህ ታላቅ ታሪክ ላይ ጥልቅ ዝርዝር አያቀርብም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ስለታሪኩ ዝርዝር ሐተታ ያቀርባል፡፡ በተውራት ውስጥ እንዲህ እናነባለን፡፡ “ከዚህ ሁሉ በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ “አብርሃም!” አለው። እርሱም “አቤቱ አለሁ” አለ። እግዚአብሔርም፣ “የምትወድደውን አንዱን ልጅህን፣ ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እኔ በማመለክትህ በአንዱ ተራራ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው” አለው። በማግስቱም ጧት አብርሃም ማልዶ ተነሣ፤ አህያውን ጭኖ፣ ሁለት አገልጋዮቹንና ልጁን ይስሐቅን ይዞ፣ ለመሥዋዕት የሚበቃውን ዕንጨት ከቈረጠ በኋላ እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጕዞውን ጀመረ፤ በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ቦታውን ከሩቅ ተመለከተ፤ አገልጋዮቹንም “እናንተ አህያውን ይዛችሁ እዚህ ቈዩን፤ እኔና ልጄ ግን ወደዚያ ሄደን ለእግዚአብሔር ሰግደን እንመለሳለን” አላቸው። አብርሃም ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን ዕንጨት ወስዶ፣ ልጁን ይስሐቅን አሸከመው፤ እሳቱንና ቢላዋውንም ራሱ ያዘ። ሁለቱም አብረው ሄዱ። ይስሐቅም አባቱን አብርሃምን፣ “አባቴ ሆይ” አለው። አብርሃምም፣ “እነሆኝ፤ አለሁ ልጄ” አለው። ይስሐቅም፣ “እሳቱና ዕንጨቱ ይኸው፤ ነገር ግን የሚቃጠለው መሥዋዕት የት አለ?” ብሎ ጠየቀ። አብርሃምም፣ “ልጄ ሆይ፤ ለሚቃጠለው መሥዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል (ኤሎሂም ይሬህሎ)” አለው። ሁለቱም አብረው ጕዟቸውን ቀጠሉ። እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ወደ አመለከተው ቦታ እንደ ደረሱ፣ አብርሃም መሠዊያ ሠራ፤ በላዩም ላይ ዕንጨት ረበረበ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያው ዕንጨት ላይ አጋደመው። ከዚያም ልጁን ለማረድ እጁን ዘርግቶ ቢላዋውን አነሣ። የእግዚአብሔር (ያህዌ) መልአክ ግን ከሰማይ፣ “አብርሃም፤ አብርሃም፤” ብሎ ጠራው፤ አብርሃምም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ። እርሱም፣ “እጅህን በብላቴናው ላይ አታሳርፍ፤ ምንም ጕዳት አታድርስበት፤ እነሆ፤ እግዚአብሔርን እንደምትፈራ ተረድቻለሁ፤ ልጅህን፣ ያውም አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሳሳህምና” አለው። አብርሃም ቀና ብሎ ተመለከተ፤ በቍጥቋጦ መካከልም ቀንዶቹ የተጠላለፉ አንድ አውራ በግ ከበስተ ኋላው አየ፤ ወደዚያው ሄዶ በጉን አመጣና የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ሠዋው። ከዚህም የተነሣ አብርሃም የዚያን ስፍራ ስም፣ “እግዚአብሔር ያዘጋጃል (ያህዌ ይርኤ)” ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም ድረስ፣ “በእግዚአብሔር ተራራ ላይ ይዘጋጃል” ይባላል። የእግዚአብሔርም መልአክ አብርሃምን ከሰማይ ዳግመኛ ጠራው፤ እንዲህም አለው፤ “እግዚአብሔርም በራሴ ማልሁ አለ፤ አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሳሳህምና፣ በርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብት፣ እንደ ባሕር ዳር አሸዋም አበዛዋለሁ። ዘሮችህም የጠላቶቻቸውን ደጆች ይወርሳሉ፤ ቃሌን ስለ ሰማህ የምድር ሕዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ።” ከዚያም አብርሃም ወደ አገልጋዮቹ ተመለሰ፤ ተያይዘውም ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ ኖረ” (ዘፍጥረት 22፡1-17)::

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጻፈው ለዓለም ሁሉ መስዋዕት ሆኖ የዋጀው የአላህ መሲህ የሆነው ኢሳ አል-መሲህ (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ነው፡፡ ነቢዩ የህያ “እነሆ! የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” (ዮሐንስ 1፡29) ብሎ ተናገረ፡፡ የኢሳ መስዋዕትነት ላይ ለማተኮር ሲል በዚህ ስም ጠራው፡፡

ኢሳ አል-መሲህ (ሰላሙ በእኛ ላይ ይውረድ) አንድ ቀን ለአይሁድ ሲመልስ እንዲህ አለ፡- “አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ለማየት ተስፋ በማድረግ ተደሰተ፤ አየም፤ ሐሤትም አደረገ” (ዮሐንስ 8፡56)። ነቢዩ ኢብራሂም የኢሳ አል-መሲህን መምጣትና ታላቅ መስዋዕት በመሆን ዓለምን እንደሚያድን በተስፋ ይጠባበቅ ነበር፡፡ በይስሐቅ መስዋዕትነት ውስጥ እንደጥላ የተገለጠው አዳኝ እርሱ ነው፡፡

ኢብራሂም የኢሳን (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) መስዋዕትነት ቀደም ብሎ አይቷል፡፡ ኢብራሂም ለአላህ ካለው ታላቅ ፍቅርና መታዘዝ የተነሳ የገዛ ልጁን መስዋዕት አድርጎ ማቅረቡን ሙስሊሞች በየዓመቱ ይዘክራሉ፡፡ ነገር ግን እውነተኛ አማኞች ዓመቱን ሙሉ በየቀኑ አላህ ለሰዎች ሁሉ ያሳየውን ፍቅር፣ ቃሉና መንፈሱ የተባለውን፣ ኢሳ አል-መሲህ የምንለውን አሳልፎ በመስጠት ወደር የሌለውን ፍቅሩን እንደገለጠልን እንደሚዘክሩ ያዉቃሉ? “ክርስቶስ የብዙ ሰዎችን ኀጢአት ለመሸከም፣ እንዲሁ አንድ ጊዜ መሥዋዕት ሆኗል፤ ሁለተኛ ጊዜም ይገለጣል፤ ይህም ለሚጠባበቁት ድነትን ለማምጣት እንጂ ኀጢአትን ለመሸከም አይደለም” (ዕብራውያን 9፡28)።

More Stories
What Does “The Son of God” Mean?
አማርኛ