1. ኢሳ አል-መሲህ (ሰላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ማን ስለመሆኑ መወሰን፡፡ “ኢየሱስም እንዲህ አለው፡- መንገዱ እኔ ነኝ፣ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሐንስ 14፡6)፡፡ 2. አላህን በሙሉ ልብና ሃሳብ መውደድ፡፡ “እርሱም እንዲህ አለው - ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ” (ማቴዎስ 22፡37)፡፡ 3. ሐጢአትንና አለማዊነትን ማሸነፍ - “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ፤ ከእንግዲህ እኔ አልኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በውስጤ ይኖራል። አሁንም በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለኝ እምነት ነው” (ገላቲያ 2፡20)። 4. ሁሉንም ለእርሱ ማስረከብ - ““ኑና እንዋቀሥ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ኀጢአታችሁ እንደ ዐለላ ቢቀላ፣ እንደ በረዶ ይነጣል፤ እንደ ደም ቢቀላም፣ እንደ ባዘቶ ነጭ ይሆናል” (ኢሳያስ 1፡18)። 5. ሙሉ በሙሉ መቀደስ - “እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኳችሁ ነው” (ሮሜ 12፡1)፡፡ 6. በየቀኑ ከእርሱ ጋር መራመድ - “እንግዲህ ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት እንዲሁ በእርሱ ኑሩ፤ 7በእርሱ ተተክላችሁና ታንጻችሁ እንደ ተማራችሁት በእምነት ጸንታችሁ፣ የተትረፈረፈ ምስጋና እያቀረባችሁ ኑሩ” (ቆላሳይስ 2፡6-7)።