ኢሳን (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) በህልም ማየት እውነተኛ መገለጥ ነው፡፡ እብን ሲሪን እንደነገሩን ኢሳን (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) በህልሙ የሚያይ ሰው (ወንድ) ከሌሎች ሰዎች ይልቅ መልካምና የሚጠቅም ሰው ነው፤ የተባረከም ነው፤ በመሆኑም ለሌሎች መልካም ለማድረግና ሊጠቅማቸው ወደ ብዙ ቦታ ይጓዛል፡፡ አንዲት ልጃገረድ ኢሳን (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) በህልም ማየት መልካም የምታደርግና ሌሎችን የምትጠቅም በመሆን መልካሙን መንገድ የምትከተል እንደምትሆን ያሳያል፡፡ እርጉዝ ሴት ኢሳን (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) በእሻራ ካየች ጠቢብ የሆነና መልካም ለማድረግ ሃይልና ስልጣን ያለው ወንድ ልጅ እንደምትወልድ ያመላክታል፡፡ ላገቡና እንደዚሁም ለሌሎች ሴቶች ደግሞ፤ ልጅ የመውለድ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ከሆነ እንደሚያረግዙ ያሳያል፤ ለሌሎች ሴቶች ደግሞ ደስተኛ እንደሚሆኑና እርካታ እንደሚያገኙ ያሳያል፡፡
ሌሎች ፈሳሪዎች ደግሞ ወንዶችና ሴቶች ኢሳን (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) በህልም ካዩ ከአላህ በረካ የመቀበል ምልክት ወይም በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ላለ ሰው እንክብካቤ እንደሚያደርግ የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ የእርሱ (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) በህልም በአንድ ሥፍራ ላይ መውረድ ፍትህ በዚያ ሥፍራ እንደሚሰፍን፤ በረከት እንደሚወርድ፣ አላማኞች እንደሚሸነፉና ሙኢሚንኖች ደግሞ እንደሚያሸንፉ የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡
ኢሳን (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) በእሻራ ማየት ከዚህም የዘለለ ትርጉም አለው ማለት እንችላለን፡፡ ብዙዎችን ለማዳን ነው የመጣው፡፡ በህልም መገለጡ በአጠቃላይ ለሰብአዊ ሰው ሁሉ ለነፍስ ሰላም ያመጣል፡፡ ከአላህ ለራቀች ነፍስ የእርሱ መገለጥ ተስፋን ያለመልማል፡፡ መገለጡ ፍርሃትን ያስወግዳል፡፡ የእርሱ መገለጥ ደህንነትን ያውጃል፡፡
ማንም ያልሰራውን ታላላቅ ተአምራት እርሱ እንዳደረገ ቁርአን ይናገራል፡፡ ሙታንን ያዛል፤ እነርሱም ህይወት ይዘራሉ፡፡ ለአይነስውሩ የአይኑን ብርሃን ይመልስ ነበር፡፡ የለምጻሙን አካል ነክቶ አነጻው፡፡ ከጭቃ የወፍ ምስል ሰርቶ እስትንፋሱን እፍ አለበት፤ ከዚያም ህይወት ያላት ወፍ ሆነች፡፡ የማይታየውን ያውቃል፡፡ ለደረሳዎቹ ማህድ ከሰማይ እንዲወርድላቸው ጠየቀ፡፡ ሞትን ድል አድርጎ ከሙታን በመነሳት ወደ ሰማይ ተወሰደ፡፡
በተጨማሪም ቁርአን የትም ቢሆን እርሱ የተባረከ እንደሆነ፤ ለዓለማት ምህረት እንደሆነ፤ “ዛኪ” ወይም ከኃጢያት ሁሉና ከስህተት ሁሉ የነጻ እንደሆነ፤ እርሱ የአላህ ቃልና የእርሱ መንፈስ እንደሆነ፤ በዚህ ዓለም በትንቢት የተከበረ (ዋጅህ) እንደሆነና በሚመጣውም ዓለም በማማለድና በትልቅነት የተከበረ እንደሆነ እና ሁሉን ለሚችለው አምላክ ለአላህ የቀረበ እንደሆነ ይናገራል፡፡
በቁርአን ውስጥ የሚገኙ እነዚህ ሁሉ ጥቅሶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ ተጨባጭ መረጃዎች ጋር ይስማማሉ፡፡ እነዚህም ኢሳ (ሠላሙ በእኛ ላይ ይሁን) ለየት ያለ መሆኑ፣ “ኢሳ፣ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢያታቸው ያድናቸዋልና” (ማቴ 1፡21)፤ “አማኑኤል” (ትርጉሙም አላህ ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው) (ማቴ 1፡23)፤ “ስለዚህ የሚወለደው ቅዱስ ሕፃን የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል” (ሉቃስ 1፡35)፤ እና “መድህን ተወልዶላችዋልና እርሱም ጌታ ክርስቶስ (መስሁ) ነው” (ሉቃስ 2፡11) የሚሉት ናቸው፡፡
ኢንጂል አገልግሎቱን ያውጃል፡ “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌል እንድሰብክ እርሱ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩት መፈታትን፣ ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፤ የተጨነቁትን ነጻ እንዳወጣ፤ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እንዳውጅ ልኮኛል” (ሉቃስ 4፡18-19)፡፡