የነቢዩ ሱሌይማን (ሰሎሞን) ሕልሞች

ንጉሥ ዳዊት ከሞተ በኋላ ልጁ ሱሌይማን በፋንታው ነገሠ፡፡ ለአላህ ታማኝ፤ ሕግጋቱንም የሚያከብርና ፈቃዱን ለመፈጸም የሚፈልግ ሰው ነበር፡፡ አላህ የሱሌይማንን የልቡን መሻት በማየት ሕልም ሰጠው፡፡

“በገባዖንም እግዚአብሔር ለሰሎሞን ሌሊት በሕልም ተገለጠለት፤ አምላክም፣ “እንድሰጥህ የምትፈልገውን ሁሉ ለምን” አለው። ሰሎሞን እንዲህ ሲል መለሰ፤(. . .) ‘ባሪያህ አንተ በመረጥኸው ሕዝብ፣ ከብዛቱም የተነሣ ሊቈጠር በማይችል ታላቅ ሕዝብ መካከል ይገኛል። ስለዚህ መልካሙንና ክፉውን በመለየት ሕዝብህን ማስተዳደር እንዲችል ለባሪያህ አስተዋይ ልብ ስጠው፤ አለዚያማ ይህን ታላቅ ሕዝብህን ማን ሊያስተዳድር ይችላል?’ ሰሎሞን ይህን በመለመኑ ጌታ ደስ አለው፤ ስለዚህ እንዲህ አለው፤ “ለራስህ ረዥም ዕድሜ፣ ብልጽግና እንድታገኝ ወይም ጠላቶችህ እንዲጠፉልህ ሳይሆን፣ በትክክል ማስተዳደር እንድትችል ማስተዋልን ስለ ጠየቅህ፣ ይህንኑ አደርግልሃለሁ፤ ከአንተ በፊት ማንም ያልነበረውን፣ ከአንተም በኋላ ማንም የማያገኘውን ጥበብና አስተዋይ ልቡና እሰጥሃለሁ፤ ከዚህም በላይ አንተ ያልጠየቅኸውን ብልጽግናና ክብር እሰጥሃለሁ፤ ይኸውም በሕይወት ዘመንህ የሚተካከልህ ማንም ንጉሥ እንዳይኖር ነው። አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በመንገዴ ብትሄድ፣ ሥርዐቴንና ትእዛዜን ብትጠብቅ ዕድሜህን አረዝመዋለሁ።” ሰሎሞንም ከእንቅልፉ ነቃ፤ እነሆ ሕልም መሆኑን ተረዳ። ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ፣ በጌታ ኪዳን ታቦት ፊት ቆመ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ፤ ለሹማምቱም ሁሉ ግብዣ አደረገ” (1ኛ ነገሥት 3፡5-15)።

አላህ ለሱሌይማን ለመናገር በሕልም ተጠቀመ፤ በረከቱና ጥበቃውም ከእርሱ ጋር እንደሚሆን አረጋገጠለት፡፡ ጥበብ እንዲሰጠው ስለጠየቀ አላህ በጥበብ ሞላው፤ እንደዚሁም ከማንም ንጉሥ በበለጠ ሁኔታ በሃብትና በክብር አበለጸገው፡፡

ዛሬም አላህ ሊያስተምረንና ሊባርከን ሕልምን እንደሚጠቀም ይህ ሌላ ማረጋገጫ ነው፡፡

More Stories
The Uniqueness of the Bible
አማርኛ