“ ‘ወዳጅህን ውደድ፤ ጠላትህን ጥላ’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ እላችኋለሁ። እንደዚህም በማድረጋችሁ በሰማይ ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ፀሓዩን ለክፉዎችና ለደጎች ያወጣል፤ ዝናቡንም ለኀጢአተኞችና ለጻድቃን ያዘንባል። የሚወድዷችሁን ብቻ የምትወድዱ ከሆነ ምን ዋጋ ታገኛላችሁ? ቀራጮችስ ይህንኑ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁን ብቻ እጅ የምትነሡ ከሆነ ከሌሎች በምን ትሻላላችሁ? አሕዛብስ ይህንኑ ያደርጉ የለምን? ስለዚህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ” (ማቴዎስ 5፡43-48)።
አላህ ፍቅር ነው፤ አላህ ምስጢርም ነው፡፡ ስራዎቹ ከእኛ ስራዎች የራቁ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እርሱ ይፈልገናል፡፡ አላህ የትየለለ ነው፣ ነገር ግን ለሰዎች በጣም ቅርብ ነው፤ ሶስት ሲሆን አንድ ነው፣ ሁሉን የሚያውቅ ነገር ግን ሁሉን ይቅር የሚችል ነው፡፡ ከአብ፣ ከወልድና ከሩሁል ቁዱስ ጋር የሚኖረንን የጠለቀ ግንኙነት ለዘለዓለም እያደነቅን እንኖራለን፡፡ ሐጢያት ከአላህ ቢያርቀንም፣ አላህ ግን በብዙ መንገዶች ራሱን ገልጦልናል፡፡
እግዚአብሔር አብ እኛን ለመድረስ የተጠቀመበት ዋነኛው መንገድ በልጁ ኢሳ አል-መሲህ ነበር፡፡ እርሱም ዝም ብሎ ሊጎበኘን ሳይሆን ከእኛ እንደ አንዱ ሊሆን መጣ፡፡ ልክ እኛ በመንፈስ መወለድ እንደምንችል፣ ኢሳም ሰው ሆኖ ተወልዶ የአላህን ፍቅርና ባሕሪይን ገለጠልን፡፡ ይሄውም፣ አላህ ከጥፋት ሊያድነን ምን ያክል ርቀት ለመሄድ ፈቃደኛ እንደሆነ ለማሳየት ነው፡፡ እኛ ለራሳችን ማድረግ ያልቻልነውን እርሱ ለእኛ አደረገልን፡፡ እኛ ለዘለዓለም እንድንኖር የሐጢያታችንን ዋጋ በመክፈል በእኛ ፋንታ እርሱ ሞተልን፡፡ በትንሳኤው ኃይል ሞትን ድል ነሳ፤ ወደ ቤታችንም ሊወስደን ተመልሶ እንደሚመጣ ቃል ገባልን፡፡
እስከዚያም ቢሆን አላህ ለብቻችን አልተወንም፡፡ ሊያበረታታን፣ ሊመራን፣ እና ለአላህ ፍቅር ምስክሮች ሆነን እንድንኖር ሊቀይረን መንፈስ ቅዱስ (ሩሁል ቁዱስ) ከእኛ ጋር ነው፡፡ ነቢያትን የመራውና ኢሳን በኃይል ያስታጠቀው፣ ኪታቦች እንዲጻፉ ያደረገውና አለምን የፈጠረው ያው መንፈስ እያንዳንዳችንን የሚያስችል ኃይል ያስታጥቀናል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቤተክርስቲያንን በመንፈሳዊ ስጦታዎችና ዝቅ በላ የአገልግሎትና ርህራሄ መንፈስ ይቀሰቅሳቸዋል፡፡
ከጓደኛ ወይም ከጎረቤት ጋር ያለንን ግጭት እንዴት መፍታት እንዳለብን ኢሳ እና ኢንጂል ምን ያስተምሩናል?
“ስለዚህ መባህን በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር በምታቀርብበት ጊዜ፣ ወንድምህ የተቀየመብህ ነገር መኖሩ ትዝ ቢልህ፣ መባህን በዚያው በመሠዊያው ፊት ተወው፤ በመጀመሪያ ሄደህ ከወንድምህ ጋር ተስማማ፤ ከዚያም ተመልሰህ መባህን ለእግዚአብሔር አቅርብ”.…(ማቴዎስ 5፡23-24)።.
አንዳንድ ጊዜ አላህን እናገለግላለን እያልን ነገር ግን ከአላህ ልጆች አንዱን እንበድላለን፡፡ ኢሳ ያስተማረው፣ አላህን ለማምለክ ስንቀርብ፣ ሌሎችን በድለን ከሆነ በመካከላችን ያለውን ጉዳይ ለማስተካከል የተቻለንን ሁሉ ስለማድረጋችን ህሊናችን ንጹህ መሆን አለበት፡፡ ይህ ማለት ግን ሁል ጊዜ ሰዎች ይቀበሉናል ማለት አይደለም፡፡ ሊጠሉን ይችላሉ፤ ነገር ግን እኛ ጉዳዩን ለማስተካከል የቻልነውን ያህል ጥረናል፡፡
የአላህ ሰዎች የአላህን ፍቅር ማንጸባረቅ አለባቸው፤ ለዚህም ነው ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር የምንጥረው፡፡ “ማንም፣ “እግዚአብሔርን እወድደዋለሁ” እያለ ወንድሙን ቢጠላ፣ እርሱ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድድ ያላየውን እግዚአብሔርን መውደድ አይችልምና” (1ዮሀንስ 4፡20) ።
ሰውን መጥላት ከባድ ችግር ነው፡፡ ሰዎችን ሳንጠላ ክፉ አካሄዳቸውንና ድርጊታቸውን ልንጠላ እንችላለን፡፡ “ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳይም የዘላለም ሕይወት እንደሌለው ታውቃላችሁ” (1ዮሀንስ 3፡15)።
ኢሳ እና ኢንጂል በሚያስተምሩት መሰረት በማንም ሰው ላይ ቂም ወይም ጥላቻ ልንይዝ አይገባም፡፡ የአላህን እውነተኛ ፍቅር ልንገነዘብና ለሌሎችም ልናንጸባርቅ ይገባል፡፡
ለበለጠ ጥናት፡-
1. ሌሎች ሰዎች ቢጠሉን እኛ ልዩ ለመሆን ፈቃደኞች መሆን አለብን፡ ሉቃስ 14፡26
2. የአላህ ፍቅር፡ - 1ዮሐንስ 4፡8
3. አላህን በመከተላችን ሰዎች ሲበድሉንና ሲጠሉን፡ ማቴዎስ 5፡10፡፡
“ኢሳ ስለ ይቅርታ ምን ያስተምረናል?”
ከዋክብት ከሰማይ ጋር እንደሚሄዱ ይቅርታ ከእግዚአብሔር ጋር ይሄዳል። ይቅር ባይ መሆን እንደማይገባን ስናውቅ በራሳችን ህይወት ለመረዳት እና ተግባራዊ ለማድረግ ይቅርታ አስፈላጊ ነው።
Iየበደላችሁን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ ይቅር ይላችኋል። ሌሎችን ይቅር ባትሉ ግን አባታችሁ ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም። ማቴዎስ 6፡14-15። Matthew 6:14-15.
ብዙ ጊዜ ይቅርታ ለማድረግ ዳተኞች ስለሆንን ይህን ጥበብ ልብ ማለታችን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የአላህን ባሕሪይ ባሳየው ኢሳ መሠረት የይቅርታ መንፈስ ሊኖረን ይገባል፡፡ ኢሳ የበደሉንን እስከ 70 X 7 (ሰባ ጊዜ ሰባት) ድረስ እንኳን ይቅር እንድንል አዞናል (ማቴዎስ 18፡21-22)፡፡