የፋጡማ ታሪክ

ስሜ ፋጡማ ይባላል፤ 21 ዓመቴ ነው፡፡ ያደኩት በኢየሩሳሌም ከተማ ሲሆን ኢስልምናን ከፍ አድርገው በሚያዩና እንደ ጸሎትና ፆም የመሳሰሉ ኃይማኖታዊ ሥርዓቶቹን በሚፈጽሙ በተማሩ ቤተሰብ ውስጥ ነው ያደኩኝ፡፡ ሙስሊም ካልሆኑ ሰዎች ጋር መነጋገር እንኳን የማልፈልግ አክራሪ ነበርኩ፡፡

በ18 ዓመቴ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ካጠናከኩ በኃላ በታላቅ ጉጉት ዩኒቨርሲቲ ገባሁ፡፡ አንድ ቀን በሥራ ቦታ እያለሁ አንድ ሰው ስለ ኢሳ አል-መሲህ ያለመውን ሕልምና ከኢስልምና ወደ ክርስትና እንደተለወጠ ነገረኝ፡፡ አሾፍኩበት፡፡ በወረቀት ላይ የታተሙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ይዞ ይዞራል፡፡ ከእጁ መነጨኩና ቀዳድጄ ጣልኳቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን አጣመዋል፤ በሶስት አማልክት ነው የሚያምኑት በማለት ክርስቲያኖችን እጠላ ነበር፡፡

አምስቱን የኢስልምና ኃይማኖታዊ ግዴታዎችን ለመፈጸም እተጋ ነበር፡፡ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ እስከ ፈጅር (የጠዋት ሶላት) የሚዘልቀውን የቂያም አል ለይል ፀሎትንም አደርግ ነበር፡፡ ሙስሊሞች በዚህ ልዩ የጸሎት ጊዜ አላህ ወርዶ ይሰማናል ብለው ያምናሉ፡፡

አንድ ቀን በቂያም አል ለይል ጸሎት አላህን እንዲህ ብዬ ጠየቅሁት፡- “አንተ ማነህ? ኢሳ አል-መሲህ ማነው?” በዚያው ሌሊት በሕልሜ ስለ ዒሳ ሄጄ ክርስቲያን ፓስተር እንድጠይቅ አላህ ነገረኝ፡፡ በነጋታው አንድ አገልጋይን አግኝቼ “ኢሳ አል-መሲህ ማነው?” ብዬ ጠየቅሁት፡፡

“እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው“ አለኝ፡፡ “በሥጋ የተገለጠ አምላክ ነው፤ የአለምን ሐጢያት የሚሸከምና ለእኛ የሞተ ነው” አለኝ፡፡

አህምሮዬ ተበጥብጦ ወደ ቤት ተመለስኩኝ፡፡ ይሄ እኮ ተራ ሕልም ነው ብዬ ራሴን ላሳምን ሞከርኩ፡፡ ለእንደዚህ ዓይነት ሕልም ስል ኃይማኖቴንና እምነቴን ልቀይር አልችልም አልኩ፡፡

በዚያ ሌሊት በቂያም አል ለይል ኢሳ ማነው ብዬ አላህን ጠየቅሁት፡፡ እንደገና ሌላ ሕልም ላከልኝ፡፡ በሕልሜም በክርስቲያን ቤተክርስቲያን ሆኜ በዒሳ ስም ስጸልይ አየሁ፡፡ አሁንም ስነቃ ይህ ተራ ሕልም ነው ብዬ ለራሴ ነገርኩኝ፡፡

በሶስተኛውም ሌሊት አላህን ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየቅሁት፡፡ “ጌታ ሆይ አንተ ማነህ?” ለሶስተኛ ጊዜ ሕልም ላከልኝ፡፡ ዒሳ አል-መሲህ በሰማይ ላይ ቆሞ እጆቹን ወደ እኔ ሲዘረጋ አየሁት፡፡ ፊቱ በጣም ያበራ ስለነበረ ሙሉ ሰማይ በፊቱ ብርሃን በራ፡፡ ነቃሁና አለቀስኩ፤ ባየሁት ነገር ከመደነቄና ከመደመመ የተነሳ ሰውነቴ ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ ቤተሰቦቼ ምን ሆነሽ ነው ብለው ጠየቁኝ፡፡ ሕልም አልሜ ነው አልኳቸው እንጂ የሕልሙን ዝርዝር አልነገርኳቸውም፡፡

በአል-መሲህ ስም መጸለይ ጀመርኩ፤ ተዓምራቶች በሕይወቴ ተከሰቱ፡፡ ብዙ ጊዜ ስሙን ስጠራ እንባዬን መቆጣጠር ያቅተኛል፡፡ ስሙ የሚያስገርም ሰላም ሰጠኝ፡፡ አንድ ሌሊት መስቀል ከአልጋዬ አጠገብ ሲታየኝ ተደነቅሁ፣ ፈራሁም፡፡ በሚቀጥለው ሌሊትም፣ በሶስተኛውም ሌሊት ክስተቱ ተደጋገመ፡፡ ወደዚያ የክርስቲያን አገልጋይ ሄጄ የገጠመኝ ነገር ነገርኩት፡፡ ከክርስቲያን ማሕበረተሰብ ጋር መጸለይ ጀመርኩኝ፡፡ እንደተሰቀለና ለእኔ እንደሞተ ዒሳ አል-መሲህ አረጋገጠልኝ፡፡

በትክክል ትዝ ይለኛል አንድ ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ የአብ፣ የወልድና የመንፈስ ቅዱስን ስም ስጠራ አንድ እንግዳ ነገር ተከሰተ፡፡ በአፌ ላይ ቀለሞች ታይተው ተመልሰው ተሰወሩ፡፡ ስለፈራሁ ለአገልጋዩ ደወልኩለት፡፡ የዳዊትን መዝሙር ካነበብን በኋላ አብረን ጸለይን፡፡ የጌታ ኃይል ተሰማኝ፤ “ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላልና” ፍርሃቴም ጠፋ፡፡

ጌታ በቀጥታ ተናገረኝ፡፡ በሕይወቴ የገጠሙኝን ነገሮች ለማመን ለብዙ ሰው ይከብደዋል፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በስሙ እየጸለይኩ በጸጋውና በምህረቱ እኖራለሁ፡፡ በሙሉ ልቤ አመልከዋለሁ፡፡ የማመልከው ስለምወደው እንጂ ስለምፈራው አይደለም፡፡ ትዕዛዛቱን እጠብቃለሁ፤ በእነርሱም እኖራለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በማንበቤ በመንፈሳዊ ሕይወቴ እያደኩ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ጌታዬ ማን እንደሆነ የበለጠ እንዳውቅና ቃሉን በጥልቀት እንድረዳ አደረገኝ፡፡ የጌታ ሴት ልጅ ለመሆን የተጠራሁ ልዩ ልጅ ሆንኩኝ፡፡

ከእኔ የሕይወት ልምምድ በኋላ ወንድሜ ጓደኛው የክርስትናን እምነት እንደተቀበለ ነገረኘ፡፡ ክርስቶስ በሕልሙ ተገልጦለት ተከተለኝ እንዳለው ነገረኝ፡፡ እንደዚሁም ክርስቶስ ለአንድ የቅርብ ጓደኛዬ በሕልም ተገለጠላት፡፡ ልቧን ለእርሱ እንድትሰጥ አሁንም አየጸለይኩላት ነው፡፡ አላህ ሁሉን በሚችለው ኃይሉና ተአምራቶቹ እንዲነካቸው ለቤተሰቦቼም እጸልያለሁ፡፡ ዛሬም በራእይና በሕልም ይናገራል፡፡

ትዕቢተኛና ልበ-ደንዳና እንደነበርኩ አልክድም፡፡ አሁን ግን ለኢሳ አል-መሲህ ታማኝ ነኝ፤ እከተለዋለሁም፡፡ ትህትናን፣ ሌሎችን መውደድንና ለእነርሱ መጸለይን አስተምሮኛል፡፡ እንድከተለውና ማዳኑን እንድለማመድ መረጠኝ፡፡ ስለወደደኝ አዳነኝ፡፡ ራስን መስዋዕት የሚያደርገው ፍቅሩ እንዴት ታላቅ ነው! የያቆብ፣ የይስሐቅና የኢብራሂም አምላክ መሃሪ አምላክ ስለሆነ ልጁን ላከልን፡፡ እንደዚሁም የሚመራንን መንፈስ ቅዱስን ላከልን፡፡

መንገድ፣ እውነትና ሕይወት የሆነውን ጌታን እንዲያውቁት ለሙስሊሞችና ለቤተሰቦቼ እጸልያለሁ፡፡ ለእርሱ ኖሬ ለእርሱ መሞት እፈልጋለሁ፡፡ በሄድኩበት ቦታ ሁሉ ስሙን አውጃለሁ፡፡ ቃሉ ከሰው ልጆች ሁሉ ቃል በላይ ነው፡፡ በፈቃዱ ሁል ጊዜ እርስዎንና እኔን ለማዳን የሚሻውን፤ በሶስት አካል የተገለጠው አንድ አምላክ ላይ ከመላእክቱ ጋር በመሆን እምነታችንን መጣል እንችላለን፡፡

More Stories
የአቤድ አል-መሲህ ታሪክ
አማርኛ