በሌሎች ላይ መፍረድ

“እንዳይፈረድባችሁ በማንም ሰው ላይ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበትም ዐይነት ይፈረድባችኋል፤ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል። በዐይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ ሳትመለከት፣ በወንድምህ ዐይን ያለውን ጕድፍ ለምን ታያለህ? በዐይንህ ውስጥ ግንድ እያለ ወንድምህን፣ ‘ዐይንህ ውስጥ ያለውን ጕድፍ ላውጣልህ’ ማለት እንዴት ትችላለህ? አንተ ግብዝ፤ አስቀድመህ በዐይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ፤ ከዚያም በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጕድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ” (ማቴዎስ 7፡1-5)።

ሰማይ ካለ ክዋክብት እንዳሉ ሁሉ፤ አላህ እስካለ ድረስ ይቅርታ አለ፡፡ ይቅርታን መረዳትና በሕይወታችን መተርጎም አስፈላጊ ነው፡፡ ሰማይ ካለ ክዋክብት እንዳሉ ሁሉ፤ አላህ እስካለ ድረስ ይቅርታ አለ፡፡ ይቅርታን መረዳትና በሕይወታችን መተርጎም አስፈላጊ ነው፡፡

“እናንተ የበደሏችሁን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ ደግሞ እናንተን ይቅር ይላችኋል። ነገር ግን የሰዎችን ኀጢአት ይቅር የማትሉ ከሆነ፣ አባታችሁም ኀጢአታችሁን ይቅር አይልላችሁም” (ማቴዎስ 6፡14-15)።

ብዙ ጊዜ ይቅርታ ለማድረግ ዳተኞች ስለሆንን ይህን ጥበብ ልብ ማለታችን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የአላህን ባሕሪይ ባሳየው ኢሳ መሠረት የይቅርታ መንፈስ ሊኖረን ይገባል፡፡ ኢሳ የበደሉንን እስከ 70 X 7 (ሰባ ጊዜ ሰባት) ድረስ እንኳን ይቅር እንድንል አዞናል (ማቴዎስ 18፡21-22)፡፡

More Stories
The Message of Peace in Isa’s Teachings